ጣና ሐይቅ እና በዙሪያው ያሉ ደሴቶች በዩኔስኮ ሊመዘገቡ ነው

Date:

የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጣና ሐይቅን እና በዙሪያው ያሉ ደሴቶችን በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በቀጣይ ዓመት እንደሚመዘገብ ለአሐዱ አስታውቋል።

የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ምክትል ቢሮ ኃላፊ አባይ መንግስቴ ሐይቁ እስካሁን በብዝሃ ሕይወት ሀብቱ ስብጥር በዩኒስኮ ተመዝግቦ መቆየቱን አስታውሰው፤ “በዓለም አቀፍ ደረጃ ሦስተኛ የተፈጥሮ ቅርስ ሆኖ እንዲመዘገብ የቅድመ ዝግጅት ሥራ አጠናቀናል” ሲሉ ገልጸዋል።

“ይህ ሀብት በዩኔስኮ ሲመዘገብ ከሰሜን ብሔራዊ ፓርክ ቀጥሎ ሁለተኛ የተፈጥሮ ሀብት ሆኖ በክልሉ ይመዘገባል” ሲሉም አስረድተዋል፡፡

በአገር አቀፍ ደረጃ ጂኦ ፓርክ እና ጂኦ ቱሪዝም ጋር በተያያዘ ለጂኦ ፓርክ የሚሆኑ ቦታዎች በክልሉ የሚገኙ መዳረሻ ቦታዎች የመለየት ሥራ እንደ አዲስ እየተሰራ መሆኑንም ምክትል ቢሮ ኃላፊው ገልጸዋል።

ክልሉ በዚህ ዓመት 5 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ከቱሪዝም ገቢ ማግኘት መቻሉን አስታውቋል።

በክልሉ ከሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎች አንፃር በቂ አለመሆኑን ያነሱት ኃላፊው፤ “ክልሉ የሚገኝበት ነባራዊ ሁኔታ የተሻለ ገቢ እንዳይመዘገብ አድርጎል” ሲሉ ገልጸዋል።

በአጠቃላይ በዚህ ዓመት 9 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሰዎች ለጉብኝት ወደ ክልሉ መግባታቸውንም ጨምረው ተናግረዋል፡፡

ጣና ሐይቅ በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ በአማራ ክልል የሚገኝ ሐይቅ ሲሆን፤ በስፋቱም በኢትዮጵያ ቀዳሚ ሐይቅ ነው።

በሐይቁ ውስጥ በቋጥኝ እና በደን የተሸፈኑ ከ37 በላይ ደሴቶች የሚገኙም ሲሆን፤ ከእነዚህ ውስጥ 20ዎቹ ታሪካዊ ገዳማትን እና አድባራትን ይዘዋል፡፡

(አሐዱ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

‹‹ማንም ሰው ጋር ጠባሳ መተው አልፈልግም››አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ

ግዮን መጽሔት :- ውድ የግዮን መጽሔት አንባብያን፣ በቅርቡ...

ውጭ ምንዛሪ የሚያድኑ የሴራሚክ ምርቶች በቅርቡ ለገበያ ይቀርባሉ

ይህ የተገለፀው ኢትዮደር ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በ”Golden Tier...