የአሜሪካ እና የሩስያ ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ውይይት አደረጉ

Date:

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ እና የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በማሌዥያ ኩዋላ ላምፑር በተካሄደው የእስያ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ እንደገና ተገናኝተዋል።

የሩሲያ መንግስታዊው ታስ የዜና ኤጀንሲ እንደዘገበው ውይይቱ በዩክሬን ውስጥ ያለው ጦርነት ዋናው ትኩረት ነበር ብሏል። በትላንትናው እለት በሁለቱ ከፍተኛ ዲፕሎማቶች መካከል የተደረገውን የ50 ደቂቃ ቆይታ እንደነበረም ተሰምቷል።

ከዲፕሎማቾቹ ውይይት በኃላ ምንም ዝርዝር መረጃ እስካሁን ባይወጣም ሩቢዮ ሐሙስ እለት ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ሁለቱ ወገኖች በዩክሬን ላይ የሰላም ጥረትን ለመድረስ “አዲስ እና የተለየ አቀራረብ” በሚለው ላይ ተወያይተዋል። “ሰላሙን የሚያረጋግጥ ነገር አድርጌ ልገልጸው አልችልም ነገር ግን ወደ ፕሬዝዳንቱ የምመልሰው ጽንሰ-ሃሳብ ነው” ብለዋል።

ላቭሮቭ አርብ ዕለት ጦርነቱን ለመፍታት የክሬምሊን አቋም እንዳስቀመጡ ተናግረዋል ። በዩክሬን ጉዳይ ላይ ተወያይተናል ፤ በዚህም በጁላይ 3 ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ያደረጉትን ውይይት ጨምሮ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን የገለፁትን አቋም አረጋግጠናል።

“በማለት ላቭሮቭ ለሩሲያ ሚዲያ ተናግረዋል። የሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ዲፕሎማቶቹ በዩክሬን እንዲሁም በኢራን፣ በሶሪያ እና በሰፊ አለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ “ተጨባጭ እና ግልጽ ውይይት” አድርገዋል ብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...