በጦርነት እየተናጠች የምትገኘው ዩክሬን  ጠቅላይ ሚኒስቴር  ሾመች

Date:

ከሩሲያ ጋር በአውዳሚ ጦርነት ውስጥ የምትገኘው ዩክሬን ከአምስት ዓመታ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የዩሊያ ስቪሪደንኮን የሀገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር በማድረግ በዛሬው ዕለት ሾማለች፡፡

የሀገሪቱ ፓርላማ ከሩሲያ ጋር ይደረሳል የተባለው የሰላም ስምምነት ተስፋ እየደበዘዘ መምጣቱን ተከትሎ፤ የጦር ጊዜ አስተዳደርን ለማደስ እያከናወነ የሚገኘው ዋና የካቢኔ ማሻሻያ አካል የሆነውን የጠቅላይ ሚኒስትሯን ሹመት በ262 ድምጽ አጽድቆታል፡፡

ይህም በዩክሬን የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ የተረከቡ ሁለተኛዋ ሴት መሪ አድርጓቸዋል፡፡

የ39 ዓመቷ የዩክሬን ጠቅላይ ሚኒስቴር ዩሊያ ስቪሪደንኮ፤ የሀገር ውስጥ የጦር መሳሪያ ምርትን የማሳደግ፣ የዩክሬንን ኢኮኖሚና ማህበራዊ አቅም የማጠናከር እንዲሁም የዩክሬናውያንን የድጋፍ ፕሮግራሞች የማስፋፋት ተልዕኮ ከፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ተሰጥቷቸዋል፡፡

ዘሌንስኪ ለፓርላማ ባደረጉት ንግግር፤ አዲሱ መንግሥታቸው በዩክሬን የጦር ሜዳ ላይ ያለውን የሀገር ውስጥ መሳሪያ ድርሻ በስድስት ወራት ውስጥ ከ 40 በመቶ ወደ 50 በመቶ ያሳድጋል ብለው እንደሚጠብቁ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

እ.ኤ.አ. ከ2021 ጀምሮ ተቀዳሚ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የኢኮኖሚ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉት የዩሊያ ስቪሪደንኮ በበኩላቸው ከሹመታቸው በኋላ ባደረጉት ንግግር፤ “በፍጥነት እና በቆራጥነት” ለመስራት ቃል ገብተዋል።

በኤክስ ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍም፤ “ጦርነት ለመዘግየት ቦታ አይሰጥም” ሲሉ ጽፈዋል።

“ለመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ቅድሚያ የምንሰጣቸው ጉዳዮች ግልጽ ናቸው፡፡ ለሠራዊቱ አስተማማኝ አቅርቦት፣ የአገር ውስጥ የጦር መሣሪያ ምርትን ማስፋፋት እና የመከላከያ ሰራዊታችንን የቴክኖሎጂ ጥንካሬ ማሳደግ ናቸው” ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ስቪሪደንኮ የዩክሬን ማዕድን ሀብት ለአሜሪካ የሚሰጥ ስምምነት ላይ በመደራደር በትራምፕ አስተዳደር ዘንድ በደንብ የሚታወቁ ሲሆን፤ ይህም በኪዬቭ እና በዋሽንግተን መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ወሳኝ ስለመሆኑ ተመላክቷል።

(አሐዱ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

“ቴዲ አፍሮ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ቀይሮታል!” — ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

በ"ወቸው ጉድ" ፖድካስት ላይ እንግዳ ሆነው የቀረቡት ፕሮፌሰር ብርሃኑ...

የኢራን ጦር የሆርሙዝ ወሽመጥን በድጋሚ መዝጋቱን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ

የኢራን መገናኛ ብዙኃን የአገሪቱ ጦር የሆርሙዝ ወሽመጥን ዳግም መቆጣጠር...

ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል 20ኛ ዓመት ክብረ በዓል

ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል 20ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አስመልክቶ...

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለ20 አትሌቶች  የማስጠንቀቂያ አውጥቷል

በውድድሩ ላይ ያልተገኛችሁ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይመለከታል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዓለምአቀፍ...