የቀድሞዉ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በሀገር ክህደት ወንጀል ያለምንም ማስረጃ ተከሰሱ

Date:

ክሱን ያቀረቡት ደግሞ የአሁኑ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ናቸዉ፡፡ ጉዳዩን ክህደት ነው በማለት የገለፁት ፕሬዘዳንቱ ሰዎቹን ለመከታተል ጊዜው አሁን ነው ሲሉም ተናግረዋል።

የቀድሞውን ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማን፣ ፕሬዝዳንታዊ እጩ የነበሩትን ሂላሪ ክሊንተንን፣የቀድሞው የኤፍቢአይ ዳይሬክተር ጄምስ ኮሚንን እና የቀድሞው የብሔራዊ መረጃ ዳይሬክተር ጆን ብሬናን ጨምሮ ሌሎችም በእኔ ላይ አሲረዋል ሲሉ ከሰዋል።

ትራምፕ በ2016 በተካሄደው የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዴሞክራቷን እጩ ሂላሪ ክሊንተንን በማሸነፍ 45ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው መመረጣቸው ይታወሳል።

ምንም እንኳን ፍርድ ቤቶች፣ የየግዛት መንግስታት እና የራሳቸው የቀድሞ አስተዳደር አባላት ሳይቀሩ የትራምፕን የይገባኛል ጥያቄ ውድቅ ቢያደርጉትም፤ ትራምፕ በ2020 ምርጫ የተሸነፉት በድምፅ ስርቆት እንደሆነ እንደሚያምኑ ገልጸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ

ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ዕድገት ወደር የሌለው አስተዋጽኦ ላበረከተውና የሙዚቃው...

ሕወሓት ድብረጺዮንን የክልሉ ፕሬዚዳንት አድርጎ መረጠ

የክልሉ ፕሬዚዳንት ተደርገው የተመረጡት  ድብርጺዮን ገ/ ሚካዔል (ዶ/ር)  ቃለ...

” ኢራን ከምድረ ገጽ ትጠፋለች ” – ትራምፕ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፎክስ ኒውስ ቴሌቪዥን ጋር ቃለ...

የአርበኞች ድል መታሰቢያ እና የዛሬው ትውልድ ለሕብረት ያለው አቋም

የጥንት ኢትዮጵያዊያንአርበኞች ድል 85 ኛው ዓመት መታሰቢያ ሚያዚያ...