የሰውን ህልም የምታበላሹ ሰዎች ፈጣሪ የስራችሁን
ይስጣችሁ !!!
ጋዘዜጠኛ ሶፎንንያስን እናግዘው !
Share ሼር በማድረግ ለደጋግ ኢትዮጵያኖች አድርሱ 🙏
ይህ ጠንካራ ብዙ ህልም የነበረው ጋዜጠኛ ባመነው
ጓደኛው ተከድቶ ህይወቱን አመሰቃቅሎበታል።
ጋዜጠኛ ሶፎንያስ ዋስይሁን ኑሮን ለማሸነፍ ፦
የታክሲ ረዳት ፣ የፓርኪንግ ሰራተኛ ፣ ማስቲካ በማዞርና
በመሸጥ ፣ እንዲሁም ሊስትሮ ሆኖ ሰርቷል።
የሊስቶሮ ዕቃውን አሁንም ድረስ ቤቱ አስቀምጦታል።
መምህራን ኮሌጅ በቲቺንግ ተመርቆ 6 ዓመት በመምትርነት
አገልግሏል።
etv የወጣቶች ፕሮግራም ላይ በነፃ ልስራ ብሎ ጠይቆ
ተፈቅዶለት ልምድ ቀስሞ ወጥቷል።
በመቀጠል የኮካኮላ ሱፐር ስታርስ አይዶል ሾው ላይ
በብቃት እያስተዋወቀ መድረክ መርቷል።
Jtv ኢትዮጵያ ቲቪ ላይ የመዝናኛ ዜና በብቃት በመምራትም
ይታወቃል። አቀራረቡም ተወዳጅ ነበር።
በመጨረሻም ብዙ ዓመታት ወደአገለገለበት etv በመመለስ
የእሑድ መዝናኛ ፕሮግራምን በቀጥታ ስርጭት በብቃት
መርቷል።
በርካታ አርቲስቶችን እና ሌሎች ሰዎችን በቀጥታ ስርጭች
ቃለ – ምልልስ በብቃት የመራ አንበሳ የመዝናኛ ፕሮግራም
አቅራቢ ነው።
በመሐል ለዚህ የጭንቀት በሽታ የዳረገው ነገር ተፈጠረ።
ከፍተኛ ገንዘብ አገኝበታለሁ ብሎ ያሰበው አንድ የበዓል ፕሮግራም ለመስራት ከሚያምነው ጓደኛው ጋር ተዋውሎ
እስከዛሬ ለፍቶ ያፈራውን ገንዘብ አሟጦ ለዚህ ጓደኛው
ሰጠው።
ይኼ ጓደኛው ለበዓል የተቀረፀውን ፕሮግራም ኤዲት ሳያደርገው ክፍለ ሀገር ትቶት ሄደ።
ጋዜጠኛ ሶፎንያስም የለፋበት ፣ የደከመበት እና ብዙ ገንዘብ
ወጪ አድርጎበት የነበረው ስራ ሲበላሽበት ጭንቀት ውስጥ
ገባ።
በጭንቀት በሽታ ለ1 ዓመት በፀበልና በሕክምና ሲረዳ
ቆይቶ አሁን ወደ ቀድሞ ጤናው ለመመለስ እያገገመ ይገኛል።
ይኼ ቀልጣፋ የሚችል የመዝናኛ ፕሮግራም አቅራቢ
ነሐሴ 15/2017 በትርታ Fm 97.6 Fm ራዲዮ ላይ
ማለፊያ የተሰኘ የመዝናኛ ፕሮግራም ዘወትር ሐሙስ
ከቀኑ 9 – 11 ሰዓት ከባልደረቦቹ ጋር ይዞ ለመምጣት
ዝግጅቱን አጠናቋል።
ጋዜጠኛ ሶፎንያስ ዋስይሁንን ለመርዳትና ለማገዝ
የምትፈልጉ ደጋግ ኢትዮጵያውያን ወገኖች ሁሉ ፦
የጋዜጠኛ ሶፎንያስ ዋስይሁን ስልክ ቁጥር ፦
0910-72-44-27
CBE – 1000035113286
በገንዘብ መርዳት የማትችሉ ወገኖች
Share ሼር በማድረግ ተባበሩ 🙏
Sofonyas Wasihun አንተ አንበሳ የመዝናኛ ፕሮግራም አቅራቢ ነህ። መንፈሰ ጠንካራ እንደሆንክም አውቃለሁ።
የትኛውም የቲቪ ጣቢያዎች ለመዝናኛ ፕሮግራም አቅራቢነት
ተሻምተው ሊወስዱህ የሚገባህ አንበሳ ጋዜጠኛ ነህ።
አንተ በስራ ዘመንህ በርካቶች እንዲረዱ እና እንዲደገፉ ያደረግህ ሰው ነህና ሕዝቡም ይኽንን ውለታህን እንደሚመልሰው አልጠራጠርም።
በአጭር ጊዜ ከፈጣሪ በወገኖችህ እገዛና በፈጣሪ እርዳቻ
ታግዘህ ወደ ቀድሞው ቦታህ እንደምትመለስ አምናለሁ።
ሶፊዬ እንኳን ተሻለህ። በርታ ! ጠንክር ! ወደፊት 💪
አክባሪህና አድናቂህ
ዘሪሁን ተዝናኑ
ሞቅ ካለ የሚነበብ ፊርማ ጋር !!!
