አንድ ኮሎምቢያዊ ገበሬ 600 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ተቀብሮ አገኘ

Date:

የኮሎምቢያ ሚዲያን ዋቢ በማድረግ ማርካ የተባለ የየቀን ጋዜጣ ድረ-ገፅ ከቀናቶች በፊት እንደዘገበው አንቲዮኪያ በተባለ ቦታ የተገኘው ገንዘብ ማንነቱ እንዳይገለጽ የፈለገው ገበሬ፣ የእርሻ ቦታውን ሲያሰፋ ከመሬት አንድ ሜትር በላይ ጥልቀት ላይ የተቀበሩ በርካታ የዛገ የብረት በርሜሎች አገኝቷል።

በርሜሎቹ በመቶዎች የሚቆጠሩ በጥቅል የታሰሩ በዋነኝነት የአሜሪካ ዶላር የባንክ ኖቶች የያዙ ሲሆን፣ እነዚህም በጥሩ ሁኔታ ተጠብቀው ተገኝተዋል።

የኮሎምቢያ ባለስልጣናት ግኝቱ እንደተነገረ ወዲያውኑ ገብተው የገንዘቡን ትክክለኛ ምንጭ ለመወሰን ምርመራ ጀመሩ። የመጀመሪያው ግምት እንደሚያሳየው፣ ገንዘቡ የ1980ዎቹ እና 1990ዎቹ የሜደሊን ካርቴል ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ በቀላሉ ህጋዊ ማድረግ ወይም ማንቀሳቀስ ስላልተቻለ ለማከማቸት ይጠቀሙባቸው ከነበሩት መደበቂያዎች አንዱ ሊሆን ይችላል ተብሏል።

ይህ የፓብሎ ኤስኮባር ገንዘብ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘበት አይደለም። ዝናው በከፍተኛ ደረጃ በነበረበት ጊዜ፣ የአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪው ራሱ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ በእርሻ ቦታዎችና በጫካ ውስጥ ደብቆ ነበር። ከእነዚህ ውስጥ ብዙዎቹ በ1993 ከሞተ በኋላ ተረስተው ነበር።

ይህ ግኝት ስለ አፈ ታሪካዊው “ፓብሎ ኤስኮባር ሀብቶች” ፍላጎትን እንደገና አነሳስቷል፣ ነገር ግን የገበሬውን እና የቤተሰቡን ደህንነት በተመለከተም ስጋትን ፈጥሯል።

የጉስታቮ ፔድሮ መንግስት አሁን ገንዘቡን መውረስ ወይም ለገበሬው ሽልማት መስጠት እንዳለበት እያጤነ ነው።

fp

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...