የሩሲያ የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሩ ማክሲም ሬሽትኒኮቭ ከኢትዮጵያ የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ ጋር በቪዲዮ ኮንፍረንስ ተወያይተዋል።
ሁለቱ ሚኒስትሮች በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለውን ትብብር እና አጋርነት ለማጠናከር ስለሚያስችሉ ጉዳዮች መምከራቸው ተዘግቧል።
እንደ ሩሲያው የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለው የንግድ ፍሰት እየጨመረ ሲሆን ባለፈው አመት ከነበረው አንፃር በዘንድሮ ስድስት ወራት ያለው የንግድ ፍሰት ከሁለት እጥፍ በላይ ጨምሯል።
ባለፉት ስድስት ወራት በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለው የንግድ ፍሰት 191 ሚሊየን ዶላር ተሻግሯል ያሉት ሚኒስትሩ ለዚህ የንግድ ፍሰት መጨመር ምክንያቱ በዋነኝነት ሃገራቸው ከኢትዮጵያ የምታስገባው የቡና ምርት መጨመር መሆኑን አንስተዋል።
ሚኒስትሩ አክለውም የሩሲያ አምራቾች ማዳበሪያ እና የግብርና ማሽኖችን ለኢትዮጵያ ለማቅረብ ዝግጁ መሆናቸውን አንስተዋል።
tikvahethmagazine
