የህፃናት ግድያ በአሜሪካን ሚኒያ ፖሊስ

Date:


በአሜሪካን ሚኒያፖሊስ በሚገኝ የካቶሊክ ትምህርት ቤት በተከፈተ የተኩስ ጥቃት ሁለት ህፃናት ሲገደሉ 17ት የሚሆኑት ደግሞ ስለመቁሰላቸው ተሰምቷል።

በሚኒያፖሊስ የካቶሊክ የህፃናት መማሪያ ትምህርት ቤት ሆን ተብሎ በተከፈተው በዚህ ተኩስ ከቆሰሉት ውስጥ 14ቱ ህፃናት ናቸው፤

ህፃናቱ በደረሰባቸው ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት ውስጥ ናቸውም ተብሏል።

በጥቃቱ ህይወታቸው ያለፈው ህፃናት የ8 እና የ10 አመት ታዳጊ እንደነበሩ ተገልጿል።

ተኩሱን ከከፈቱት አንደኛው ሮቢን የተሰኘ የ23 አመት ወጣት ሲሆን ከዚህ ቀደም ምንም አይነት የወንጀል ሪከርድ እንደሌለበት ተረጋግጧል።

ጥቃቱን ከፈፀመ ኋላ እራሱ ላይ እርምጃ በመውሰድ ብቻውን የተፈፀመ ጥቃት እንዲመስል አድርጓልም ብሏል ፖሊስ፤

ጥቃቱ በተፈፀመት በዚህ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርት ቤት ከ5 እስከ 14 አመት የእድሜ ክልል የሚገኙ ህፃናት የሚማሩበት ነው፤

ወጣቱ ጥቃቱን የፈፀመት ምክንያት ፖሊስ እስካሁን አለመረጋገጡን አስታውቆ ሆን ተብሎ ስለመደረጉ ግን ገልጿል።

በአሜሪካ በየአመቱ መሰል በህፃናትና በሌሎችም ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች በርካታ ስለመሆናቸው ቁጥራዊ መረጃዎች ያሳያሉ።

ዘገባው የሮይተርስ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...