የኢትዮጵያ መንግስት እና ዳንጎቴ ግሩፕ ስምምነት ተፈራረሙ

Date:

የኢትዮጵያ መንግስት የኢንቨስትመንት ክንድ የሆነው ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH) እና የዳንጎቴ ግሩፕ በጎዴ ለሚገነባው የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ ትልቅ የባለአክሲዮኖች ስምምነት ተፈራረሙ።

ዛሬ የተደረገዉ ስምምነቱ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ 40 በመቶ ድርሻ ሲይዝ፣ የዳንጎቴ ግሩፕ ደግሞ ቀሪውን 60 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ እንደሚይዝ ያመላክታል።

​የፋብሪካው ፕሮጀክት አጠቃላይ ወጪ 2.5 ቢሊዮን ዶላር እንደሚሆን የተገመተ ሲሆን፣ ዓመታዊ የማምረት አቅሙም እስከ 3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። ይህ ፕሮጀክት ከተጠናቀቀ በኋላ በዓለም ላይ ካሉ ትላልቅ የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካዎች መካከል አንዱ ይሆናል።

​የፋብሪካው ግንባታ ከጀመረ በኋላ በ40 ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ከቃሉብ እና ሂላላ ጋዝ ማሳዎች ጋዝን ለማጓጓዝ የሚያስችል የቧንቧ መስመር ዝርጋታን ጨምሮ ተጨማሪ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችንም ያካትታል።

​​ይህ ፕሮጀክት የአገር ውስጥ ጋዝ ክምችቶችን በመጠቀም የማዳበሪያ ዋጋን ተወዳዳሪ በማድረግ፣ የግብርና ምርታማነትን እንደሚያሳድግ እና ኢትዮጵያን በምስራቅ አፍሪካ የማዳበሪያ ምርት ማዕከል እንድትሆን እንደሚያግዛት ተጠቁሟል።

CapitalNews

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...