ከ1 ሺህ 300 በላይ ሀገር በቀል የእጅ ሙያዎች ወደ ሥርአተ ትምህርት ሊገቡ ነው

Date:

እንደ ሽመና፣ የሸክላ ሙያ፣ የስጋጃ ሥራ እና ሌሎች መሰል ሀገር በቀል ሙያዎች ወደ ሥርአተ ትምህርቱ ለማስገባት መታቀዱ ተሰምቷል።

ከ1 ሺህ 300 በላይ የሚሆኑ የሀገር በቀል የእጅ ሙያዎች ወደ ሥርአተ ትምህርቱ እንዲገቡ ጥናት ተደርጎ መመዝገባቸውን፥ የቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶክተር) ተናግረዋል።

እነዚህ ዕውቀቶች በትምህርት ሥርአት ውስጥ እንዲገቡ ይደረግ እንጂ ሁሉም በመደበኛ ትምህርት የሚገቡ እንዳልሆኑ ጠቅሰው፥ በልምድ የተገኙ ክህሎቶች የምስክር ወረቀት እንዲሰጣቸው የሚደረግበት አሰራር እንደሚኖር አስረድተዋል።

ከመምህራን አንጻርም “ለሁሉም ሙያ መምህር ይኖራል ማለት አይደለም፥ አዘጋጅተን የጠበቅነው አሰልጣኝ ባይኖርም በመደበኛው ፕሮግራም የማሰልጠን ሥነ ዘዴን ወስዶ ሙያውን መልሶ እንዲያሰለጥን ይደረጋል” ብለዋል።

ስልጠና የሚጀመረው ሁሉም የሥርአተ ትምህርት ዝግጅት ሲጠናቀቅ እንደሆነና መሰል እውቀትና ክህሎት ሀገርኛ ይዘታቸውን ሳይለቁ ለማዘመን መታቀዱንም ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

(አራዳ ኤፍ ኤም)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ መስከረም 9 2019 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

-የግዮን እንግዳ አምዳችን :- ‹‹ምንጩና ጸሐፊው በማይታወቅ መረጃ መመራት አደገኛ...

ሸኽ መሃመድ አል አሙዲ ተጨማሪ 40 ሺህ ሠራተኞች እንዲቀጠሩ አቅጣጫ ሰጡ

የMIDROC Investment Group ሊቀመንበር ሼክ መሃመድ ሁሴን አል...

የወርቅ ማዕድን ሠራተኛው ከመገደላቸው በፊት ቤተሰባቸው ከታጣቂዎች ጋር ያደረገው የመጨረሻው የስልክ ምልልስ

ማስጠንቀቂያ፡ ቀጥሎ የሚያነብቡት ታሪክ ሊረብሽዎት ይችላል በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ...