የኢቲቪ ፓርላማ ቻናል ተመረቀ

Date:

ቻናሉ ስርጭት መጀመሩ ለጠንካራ የትውልድ ግንባታ የራሱ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ ሎሚ በዶ ገልጸዋል።

ሚዲያ አራተኛው የመንግሥት አካል በመሆኑ ዲሞክራሲን ማስረፅ እና ማፅናት ላይ ሚናው የጎላ መሆኑን የጠቀሱት ምክትል አፈ ጉባዔዋ፣ የኢቲቪ ፓርላማ ቻናል ሥራ መጀመሩም ለዚህ ትልቅ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።

የኢቲቪ ፓርላማ ቻናልን ለመክፈት የተለያዩ ሀገራትን ተሞክሮ መወሰዱን አንስተው፤ በተለይ ምክር ቤቶች ሚዲያን እንዴት እየተጠቀሙት ነው? የሚለው በደንብ መታየቱን ገልጸዋል።

ምክር ቤቱ አራት ትልልቅ ተልዕኮዎች እንዳሉት ጠቅሰው፣ በተለይም በዚህ የፓርላማ ቻናል የሕዝብ ተሳትፎ ሥርዓት የሚረጋገጥበት እንደሆነ ጠቁመዋል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን የተመለከተ ቻናል መኖሩ፣ የምክር ቤቱ ሥራዎች የበለጠ ተደራሽ እንዲሆኑ እና ተዓማኒነት እንዲዳብር፣ የሚወሰኑ ውሳኔዎች እና የሚወጡ አዋጆች የሚያልፉበትን ሂደት ለሕዝቡ ማሳያ ነው ብለዋል።

አክለውም ጠንካራ የሆነች ኅብረ ብሔራዊት ሀገር እንድትኖር እና ጠንካራ ሀገርን የሚገነባ ትውልድ እንዲፈጠር ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ምክትል አፈ ጉባዔ ሎሚ በዶ ተናግረዋል።
ኢቢሲ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...