በሀገራችን የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ መንደር፣ ዘርፉን ዘመኑ ወደ ሚፈልገው ዲጂታላይዜሽን ለመቀየር የረጅም ጊዜ ዝግጅት ሲያደርጉ የነበሩት 5ቱ ወጣቶች በመጨረሻም ‹‹ሪቪዚት ኢንስቲትዩሽን ኦፍ ዲዛይን አ.ማ›› የሚባል ተቋም መሥርተው ቅዳሜ ጥቅምት 8 ቀን 2018 ዓ.ም በካስፒያ ሆቴል የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ድርጅታችን ማሰልጠኛ ተቋም ሲከፍት በሀገራችን የኮንስትራክሽንና የኢንቴሪየር ዲዛይን ዘርፍ ውስጥ ያሉትን ክፍተቶች ለመሙላትና ሀገራችንም ዘመናዊ ሶፍትዌሮችን በመጠቀም ከአደጉ ሀገራት እኩል የምትራመድበትን ሒደት ለመፍጠር ያግዝ ዘንድ ብቁ ባለሙያዎችን አሰልጥኖ በሴክተሩ ያሉ ክፍተቶችን ለመሙላት ዝግጅቱን አጠናቅቋል፡፡
በተቋማችን ያሉ ባለሙያዎች በሥራው ላይ ከ10 ዓመት በላይ የቆዩና በውጪ ሀገራት ተምረው፣ በተለያዩ ተቋማት ያገለገሉ ናቸው፡፡ ሙያቸውን በተግባር ከተወጡባቸው ሀገራት መካከልም እንግሊዝ፣ ኢጣሊያ፣ የተባበሩት ዐረብ ኤመሬቶች እና ሌሎችም ሀገራት በእማኝነት ይጠቀሳሉ፡፡
ድርጅታችን የሚሠጣቸው ኮርሶች የረጅምና የዐጭር ጊዜ ሲኾኑ፣ እነርሱም፡- ቢውልዲንግ ኢንፎርሜሽን፣ ኢንቴሪየር ዲዛይን፣ አርክቴክቸራል ዲዛይን፣ ሲቪል ኢንጂነሪንግ ዲዛይን፣ ኤ.አይ(AI) እና ግራፊክስ ዲዛይን ናቸው፡፡ ኮርሶቹን ሁሉ ከዘመኑ ጋር እኩል እየተራመዱ ባሉ ሶፍትዌሮች ለማሰልጠን ተዘጋጅተናል፡፡
ሥልጠናውን ከ12ኛ ክፍል ተማሪዎች አንስቶ ዲግሪ እስካላቸው ዜጎች መውሰድ ይችላሉ፡፡ ሠልጣኞች ሥልጠናውን በማንኛውም ጊዜ ተመዝግበው መውሰድ የሚችሉ በመኾናቸው የተቀመጠ የሰዓት ገደብ የለም፡፡
በተጨማሪም የገንዘብ ችግር ላለባቸው ሠልጣኞች ከዳሽን ባንክ ጋር ባለን የሥራ ግንኙነት የክፍያውን ሁኔታ የምናመቻችበትን አሠራርም ዘርግተናል፡፡
ማስታወሻ፡- አድራሻችን ቦሌ አትላስ ግሬስ ፕላዛ 4ኛ ፎቅ ሲኾን፣ የቢሮ ቁጥራችን 011-639-32-91 የሞባይል ቁጥራችን 09-81-97-91-77 መኾኑን እንገልጻለን፡፡
