በትምህርት ቤቶች አካባቢ ተሸከርካሪዎችን ማቆም እንደሚያስቀጣ ተገለጸ

Date:

በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች አካባቢ ያለውን የትራፊክ ፍሰትን ለመቆጣጠር፤ ተሸከርካሪዎችን የሚቆሙ ግለሰቦች ላይ የገንዘብ ቅጣት እንደሚጣል የከተማ አስተዳደሩ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አስታውቋል።

በባለስልጣኑ የትራፊክ ቁጥጥር እና ሁነት አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ አያሌው አቲሳ በተሸከርካሪ ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት የሚያደርሱ ወላጆች በትምህርት ቤቶች አካባቢዎች ላይ ተሸከርካሪ ማቆም መከልከሉን የገለጹ ሲሆን፤ ይህም የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይከሰት እና አከባቢውን ከትራፊክ አደጋ ለመከላከል የተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተሸከርካሪዎች በትምህርት ቤቶች አከባቢ በመኖሩ፤ ይህንን ለመቆጣጠር የተሸከርካሪ ባለንብረቶች ተሸከርካሪያቸውን ለማቆም የመኪና ማቆሚያ ወይም ፓርኪንክን እንደ አማራጭ ሊጠቀሙ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

አክለውም ተሸከርካሪን ደርቦ እና መንገድ ዘግተው በሚቆሙ ግለሰቦች ላይ እንደ ተከሰተው የጥፋት አይነት የመቅጫ የገንዘብ እርከን ስለመኖሩ የተናገሩ ሲሆን፤ ይህንን የተላላፉ አጥፊዎች እንደ ጥፋት አይነት በገንዘብ እንደሚቀጡ ይደረጋል ብለዋል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በትምህርት ቤት አካባቢ የትራፊክ መጨናነቅ እና አደጋ እንዳይከሰት የትራፊክ ፍሰቱን ሊገድቡ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ተሰቶ እየተሰራበት እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡

በመሆኑም በትምህርት ቤቶች አካባቢ ተሽርካሪያቸውን ባለመቆም የትራፊክ ፍሰቱ ላይ ጫና እንዳይፈጠር ወላጆች የበኩላቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

አሐዱ ሬዲዮ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲና ተሳትፎ ራሳቸውን አገለሉ

የቀድሞው የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)...

ኢትዮጵያ በወጣቶች ኦሊምፒክ አራተኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር እየተካሄደ ባለው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ...

በወራቤ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ፋብሪካ በሰዓት 60 ኪዩቢክ ሜትር የማምረት አቅም እንዳለው ተገለጸ

በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመረቀው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በሰዓት...