በአርትስ ቴሌቪዥን እና በኢትዮጵያ ጃንደረባው ትውልድ መካከል የአእላፋት ዝማሬን ፣የአእላፋት ሳምንት የተሰኘውን ኤግዚቢሽን እና የጃን ፎረም መርሐግብርን በቴሌቪዥን ለማስተላለፍ ስምምነት ተፈፀመ::
አርትስ ቴሌቭዥን የ2017 የአእላፋት ዝማሬ መርሐግብርን በቀጥታ ስርጭት ማስተላለፉ ይታወሳል። ዘንድሮ የሚዘጋጀውን 3ኛውን የአእላፋት ዝማሬ በአርትስ ቴሌቪዥን እንዲሁም በአርትስ ዩቱብ ገፅ በቀጥታ ለተመልካቾቹ የሚያደርስ ይሆናል::
ከዚህ በተጨማሪ የአእላፋት ሳምንት የተሰኘ ከታኅሣሥ 16-23 ቀን 2018 ዓ.ም የሚከናወን የኤግዚቢሽንና ጃን ፎረም የተሰኘ የተለያዩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት የሚዘከሩበትና ኦርቶዶክሳዊ የምርምር ሥራዎች የሚቀርቡበት መድረክ በማኅበሩ የተዘጋጀ ሲሆን አርትስ ቴሌቭዥን ይህንን መርሐግብር የሚዘግብ ይሆናል።
ሙሉ የስምምነት ፊርማ ዝግጅቱን እና በወቅቱ የተደረጉ ገለፃዎችን ነገ ወደ እናንተ ወደተመልካቾቻችን እንደምናደርስ ለመግለፅ እንወዳለን::(አርትስ ቲቪ)
