ኤርትራ በፕሪቶሪያ ስምምነት አለመከፋቷን ገለጸች

Date:

ኤርትራ የፕሪቶርያውን የሰላም ስምምነት የማፍረስ ምንም ፍላጎት የላትም ሲሉ የኤርትራው የመረጃ ሚኒስተር አስታወቁ።
“የኤርትራ ጦር በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል አለ” የሚለውና ተደጋጋሚ የሆነ በተወሰኑ አካላት የሚነሳ ውንጀላ ፍፁም ሀሰት እና ግጭት ለመቀስቀስ ምክንያት ለመፍጠር ነው፤ የኤርትራ ወታደሮች ሙሉ በሙሉ በሉዓላዊ ግዛታቸው ውስጥ ተሰማርተው ይገኛሉ ሲሉ አቶ የማነ ገብረመስቀል ገልፀዋል።

ሚኒስተሩ አክለው ከዚህ ቀደም በብዙ አጋጣሚዎች በማያሻማ መልኩ እንደተገለጸው፣ ኤርትራ የፕሪቶሪያን የሰላም ስምምነት ለማፍረስ ምንም ፍላጎት የላትም፤ በመሰረቱም ስምምነቱ የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ነው ብለዋል።

በተመሳሳይ ኤርትራ በህወሓት የፖለቲካ አንጃዎች ውስጥ የተፈጠረውን የውስጥ ሽኩቻ የማባባስ ፍላጎት የላትም ይህም በትግራይ ህዝብ ላይ አላስፈላጊ እና ሊወገድ የማይችል ስቃይ ያስከትላል ብለዋል።

በቀይ ባህር ዙሪያ የተለያዩ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሃይሎች ሌት ተቀን የሚያወጡት የማያቋርጥ ግጭት ቀስቃሽ መግለጫዎች ለአላስፈላጊ ውጥረቱ አባባሽ ምክንያት ሆነው ቀጥለዋል ያሉ ሲሆን ይህ ያለምንም ማወላወል በጠንካራ ሁኔታ መወገዝ አለበት ሲሉም የኤርትራው የመረጃ ሚኒስተር አቶ የማነ ገብረመስቀል በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት መልእክት አስታውቀዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

“ሕገ መንግሥቱ መገንጠልን ይፈቅዳል ፤ ሕዝቡ ደግሞ ኢትዮጵያ እንድትቀጥል ዋጋ ይከፍላል”

አቶ ፍሬሕይወት ሳሙኤል(የ‹‹ሕገ መንግሥታዊ ተቃርኖዎች›› መጽሐፍ ደራሲ) ግዮን መጽሔት :-...

ባለሙያ ባልሆኑ ግለሰቦች የሚሰራጭ የተዛባ መረጃ በታካሚዎች ላይ ጉዳት እያደረሰ ነዉ

የሳይካትሪስት የሙያ ፈቃድና ሥልጠና የሌላቸው ግለሰቦች በተለያዩ መገናኛ...

የአውሮፓ ህብረት እና የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና የ1.2 ቢሊዮን ዩሮ ስምምነት ሊፈራረሙ ነው

በአውሮፓ ህብረት እና በኢትዮጵያ መካከል በሚካሄደው የንግድ ፎረም መክፈቻ...

የአዳዲስ እና የሁለተኛ ዙር መራጮች አቅምና ሚና

ግዮን መጽሔት :- በ7ኛው አገራዊ ምርጫ ላይ የአዳዲስ (ለመጀመሪያ...