ስንክሳር ዘወርኀ  ጥር ፲፪

Date:

(፳፮) በዚችም ቀን የክብር ባለቤት ጌታችንና ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ የገሊላ ክፍል በሆነች በቃና በሠርግ ቤት የሠራው የተአምራቱ መታሰቢያ ይደረግ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን መምህራን ሠሩ።

(፳፯) ቅዱስ ወንጌል እንደ ተናገረ ይህች የተአምራቱ መጀመሪያ ናት ውኃውን ለውጦ መዓዛው የሚጥም ጣፋጭ ወይን አድርጎታልና።

(፳፰) በዚህም አሳዳሪው ምስክር ሆነ ሙሽራውን በጠራው ጊዜ ሰው ሁሉ መልካሙን ጠጅ አስቀድሞ ያጠጣል ከሰከሩም በኋላ ዝቅተኛውን ያጠጣል። አንተ ግን የተሻለውን ጠጅ ወደ ኋላ አቆይተህ አጠጣህ አለው። ጌትነቱንም ገለጠ ደቀ መዛሙርቱም አመኑበት። ለርሱም ከቸር አባቱ መሐሪና ይቅር ባይ ከሆነ መንፈስ ቅዱስም ጋር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን!!

አምላከ ቅዱሳን ወይነ ቃና ፍቅሩን ያሳድርብን፤ ከድንግል እናቱና አገልጋዩ ከሚሆን ከሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ምልጃና ከቅዱሳኑ በረከት አይለየን!!

መልካም በዓል!!

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...

ትራምፕ ኢራን ላይ ያላቸው ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ጋር...