“1 ቢሊዮን ዶላር ትራምፕ ይሰጣቸው “ፑቲን

Date:

ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዶናልድ ትራምፕ “ለጋዛ የሰላም ቦርድ አንድ ቢሊዮን ዶላር ከተያዘው የሩሲያ ሀብት ይውሰዱ” አሉ።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለጋዛ ኢኒሺዬቲቭ የቀድሞ የዴሞክራቶቹ  አስተዳደር እንዳይንቀሳቀስ ካደረገው የሩሲያ ሀብት ገንዘብ እንዲወስዱ ሀሳብ ሰተዋል።

ለሩሲያ ብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት ፑቲን ሀሳቡን አቅርበዋል።

በጋዛ የሽግግር አስተዳደር ወቅት ለሚከወኑ ስራዎች ድጋፍ ፕሬዚዳንት ትራምፕ እያሰባሰቡ ሲሆን ፑቲንም ለዐለም አቀፍ ሰላም አብረን እንቆማለን ብለዋል።

ፑቲን የትራምፕን የሰላም ቦርዱን ተቀላቀሉ ጥሪ በበጎ እመለከተዋለሁ ቢሉም ቦርዱን ለመቀላቀል ግን ስትራቴጂካዊ አጋሮቻችን ጋር መምከር አለብን የሚል ሀሳብ ሰተዋል።

ለመቀላቀል ከመወሰናችን በፊትም ቢሆን ትራምፕ 1 ቢሊዮን ዶላሩን ባይደን እንዳይንቀሳቀስ ካገዱት ሀብታችን ይውሰዱ የሚል ምክረ ሀሳብም አቅርበዋል።

ሞስኮ ከፍልስጤም ህዝብ ጋር የተለየ ግንኙነት እንዳላትም አስታውሰዋል ፑቲን።

ለግብዣው ትራምፕን ያመሰገኑት ፑቲን ጉዳዩን ለማጤን ግን ክሬሚሊን ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገዋል ብለዋል።

ፑቲን ከሩሲያ ሀብት ቀንሰው ትራምፕ ለሰላም ቦርዱ ይጠቀሙ ማለታቸው ምናልባትም ሌላ ፖለቲካዊ ግርግር በአሜሪካ ኮንግረስ ውስጥ ሊፈጥር ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።

ዘገባው የአር ቲ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...