ኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ የዳንጎቴ ሲሚንቶ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተገለጸ

Date:

በአፍሪካ ግዙፉ የሲሚንቶ አምራች ዳንጎቴ ሲሚንቶ፣ በሚቀጥሉት አራት ዓመታት ውስጥ የማምረት አቅሙን በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ የሚያስችለውን የ1 ቢሊዮን ዶላር የኢንቨስትመንት ዕቅድ ይፋ አደረገ። ይህ ስልታዊ የማስፋፊያ ዕቅድ በዋነኝነት በኢትዮጵያ እና ናይጄሪያላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል።

የኩባንያው የፋይናንስ ዳይሬክተር ገቤንጋ ፋፖሁንዳ ረቡዕ ዕለት በሌጎስ በሰጡት መግለጫ፣ አዲሱ ኢንቨስትመንት የኩባንያውን የማምረት አቅም በ45 በመቶ በማሳደግ በዓመት ወደ 80 ሚሊዮን ቶን ለማድረስ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።

እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ፣ ለፕሮጀክቱ የተመደበው ፈንድ በናይጄሪያ እና በኢትዮጵያ የሚከናወኑ ግንባታዎችን ጨምሮ በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ለሚካሄዱ የማስፋፊያ ሥራዎች የሚውል ይሆናል።

ዳንጎቴ ሲሚንቶ በ ጥር ወር ‘ሲኖማ ኢንተርናሽናል’ ከተባለው የቻይና ኩባንያ ጋር በሰባት የአፍሪካ ሀገራት 12 አዳዲስ ፋብሪካዎችን ለመገንባትና ነባሮቹን ለማስፋፋት የሚያስችል የ1 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት መፈራረሙ ተገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...

የተጀመሩ የትምህርት ሪፎርሞችን በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም በቁርጠኝነት መስራት ይገባል

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን ሩብ...

የአዉሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የቡና ገበያ መዳረሻዎች እየፈለገ ነዉ

በፈረንጆቹ 2023 የፀደቀው የአውሮፓ ህብረት የደን ጭፍጨፋ ህግ ምርቶች...