በኢትዮጵያ እና በቻይና መካከል ያለውን የባህል ትስስር ለማጠናከር ያለመ የቻይና ፊልም ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በድምቀት ተከፍቷል።
እስከ መጋቢት 28 ቀን 2026 በሚቆየው በዚህ መርሃ ግብር፣ ስምንት የተመረጡ የቻይና ፊልሞች ለተመልካች እንደሚቀርቡ ታውቋል።
የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ነቢዩ ባዬ እና የቻይና አምባሳደር ቼን ሃይ በወቅቱ እንደገለጹት፤ ፌስቲቫሉ በሁለቱ ሀገራት የፊልም ባለሙያዎች መካከል የእውቀት ሽግግር ለመፍጠርና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ለማሳደግ ትልቅ ሚና ይጫወታል።
ፌስቲቫሉ የተከፈተውም የሰዎችን የጋራ ደህንነትና ልማት የሚያሳየውን “My People My Devotion” የተሰኘውን ፊልም ለእይታ በማቅረብ ነው።
