የአዲስ አበባ ፖሊስ የአመራር ለውጥ

Date:

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ባስተላለፉት ውሳኔ፣ የቀድሞው የመከላከያ የምድር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናንት ጄነራል አስራት ደኔሮን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር አድርገው ሾሙ።

ላለፉት ሰባት ዓመታት ኮሚሽነር የነበሩት አቶ ጌቱ አርጋውና ሁለት ምክትሎቻቸው ከኃላፊነት መነሳታቸውም ታውቋል።

አዲሱ ተሿሚ ሌተናንት ጄነራል አስራት፣ በመከላከያ ሠራዊት ውስጥ የመረጃ ዋና መምሪያ ኃላፊና የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት መሪ በመሆን አገልግለዋል።

በተጨማሪም በደቡብ ሱዳን የኢጋድ ተወካይና የተኩስ አቁም ቁጥጥር መካኒዝም ሰብሳቢ በመሆን የዲፕሎማሲ ልምድ አካብተዋል።

ከዋና ኮሚሽነሩ ባሻገር፣ ረዳት ኮሚሽነር ቶፊቅ መደድ እና ቀደም ሲል በአማራ ክልል የተለያዩ ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎችን ሲመሩ የቆዩት አቶ እርዚቅ ኢሳ በምክትል ኮሚሽነርነት ተሹመዋል።

መንግሥት ለሹም ሽሩ ዝርዝር ምክንያት ባይሰጥም፣ ለውጡ የከተማዋን የጸጥታ መዋቅር ለማጠናከር ያለመ እንደሆነ ይታመናል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...