የኢራን ጦር አዛዥ እስራኤል የደህንነት ኃላፊው ላሪጃኒን መግደሏን ተከትሎ ‘ወሳኝ’ የአጸፋ እርምጃ እንደሚወሰዱ ዛቱ

Date:

የኢራን ጦር አዛዥ አሚር ሃታሚ በእስራኤል የአየር ጥቃት የደህንነት ኃላፊው አሊ ላሪጃኒን መገደላቸውን ተከትሎ “ወሳኝ” የአጸፋ እርምጃ እንደሚወስዱ አስጠነቀቁ።

“ለወንጀለኛዋ አሜሪካ እና ደም የተጠማው የጽዮናውያን አገዛዝ በተገቢው ጊዜና ቦታ፣ ወሳኝ፣ የሚያሽመደምድ፣ ጸጸት ውስጥ የሚጥል ምላሽ እንሰጣለን” ሲሉ ሃታሚ በሰጡት መግለጫ ላይ ተናግረዋል።

የላሪጃኒ እና የሌሎች “ሰማዕታት ሞት እንበቀላለን” በማለት አክለዋል።

ከጦር ኃይሉ የተለየ ወታደራዊ አካል የሆነው የኢራን አብዮታዊ ዘብ የላሪጃኒን ሞት “ለመበቀል” ወደ ማዕከላዊ እስራኤል ሚሳኤሎችን መተኮሱን የኤኤፍፒ የዜና ወኪል ዘግቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ለሚገኘው ቅርንጫፉ ተጨማሪ 1.4 ቢሊዮን ሺሊንግ ኢንቨስት አደረገ

የኬንያው የቴሌኮም ግዙፍ ኩባንያ ሳፋሪኮም እስከ ሰኔ 2018 ዓ.ም...

በምክክሩ ሕዝበ ውሳኔ የተጠየቀባቸው ጉዳዮች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 15ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች በተጠናቀሩ...

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...