“የትግራይ ወጣቶች ጦርነት በቃን የሚል ድምጽ እያሰሙ ነው” አቶ ጌታቸው ረዳ

Date:


  • በትግራይ ክልል የሚገኙ ወጣቶች የኋላቀር ቡድኑን የጦርነት ጉሰማ “በቃን” በሚል ድምፅ እየተቃወሙት መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ ገለጹ።

አቶ ጌታቸው አዲስ አበባ የሚኖሩ የትግራይ ወጣቶች ባዘጋጁት የውይይት መድረክ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት፤ ትግራይ ውስጥ ያለው ወጣት አሁንም ጦርነት በቃን የሚል ድምፁን እያሰማ በመሆኑ፣ ጦርነት የሚሰብከውን ኋላቀር ቡድን “ሰላም” በሚል ቃል ልናሸንፈው ይገባል።

ባለፉት 30 ዓመታት ጦርነትን በመሸሽ የተጀመረው ስደት ወጣቶች ሀገራቸውን ጥለው እንዲሄዱ ማድረጉን ያስታወሱት አማካሪው፤ አሁን ባለው ሁኔታም በትግራይ ውስጥ ያሉ ወጣቶች ተሰድደው ለማለቅ ሦስት ዓመት የሚፈጅባቸው እንደማይመስል በመግለጽ የሁኔታውን አሳሳቢነት አብራርተዋል።

ውይይት መፍትሔ ማስገኛ ዘዴ ቢሆንም ወደ ተግባር ካልተቀየረ ልምድ ሆኖ እንደሚቀር የጠቆሙት አቶ ጌታቸው፤ የተደራጁ ሐሳቦችን ተግባራዊ በማድረግ በጦርነት ቀስቃሾች ላይ ተጽዕኖ መፍጠር እንደሚገባ አሳስበዋል።

አቶ ጌታቸው በውይይቱ ላይ የተሳተፉት ማንኛውንም ፓርቲ ወይም አደረጃጀትን ወክለው ሳይሆን፤ ትግራይን በማዳኑ ሂደት የሁሉም ድርሻ አስፈላጊ መሆኑን ስለሚያምኑ እንደሆነ ገልጸዋል።

ጦርነትን አንፈልግም የሚለው የወጣቶች ድምፅ መቐለ መሽጎ ጦርነት የሚሰብከውን ቡድን ሊያስደነግጠው እንደሚችል የገለጹት አማካሪው፤ ወጣቱ ድምፁን ይበልጥ ማሰማትና ለሰላም መደራጀት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

ጋዜጣ ፕላስ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 1 2018 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

በኢትዮጵያ ነፃ ኘሬስ ከ25 ዓመት በላይአገልግለናል !!! -የአርበኞች አደራና የትውልዱ...

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...