ተወዳጁ አሜሪካዊ የማርሻል አርት ባለሙያ እና የሆሊውድ የአክሽን ፊልም ኮከብ ቻክ ኖሪስ በ86 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተዘግቧል።
የቻክኖሪስን ሞት ይፋ ያደረጉት ቤተሰቦቹ ናቸው።
ኖሪስ ሀሙስ ዕለት በሃዋይ ግዛት በምትገኘው ካዋይ ደሴት ላይ በድንገት ታሞ ሕይወቱ ማለፉ ተዘግቧል።
“ዎከር፣ ቴክሳስ ሬንጀር” በተሰኘው ተከታታይ ፊልሙ በዓለም ዙሪያ ከፍተኛ ዝናን ያተረፈው ታዋቂው የፊልም አክተር ነበር።
በተለይም ቻክኖሪስ በቄንጠኛ የማርሻል አርት አክቲንጉ በጣም ይታወቅ ነበር።
ለመጨረሻ ጊዜ የተፋለመው ከብሩስሊ ጋር ነበር። invasion USA እና The Cutter, Agent Reckon እንዲሁም Walker በመሳሰሉት ፊልሞቹ ይታወቃል።
የቻክ ኖሪስ ቤተሰቦች በኢንስታግራም ማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባወጡት ጥልቅ የሀዘን መግለጫ፣ የተወደደው ቻክ ኖሪስ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን በከባድ ሀዘን አሳውቀዋል።
