የኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን በጌትፋም ሆቴል ባካሄደው ደማቅ መርሐግብር የ300 አዲስ የቤት እድለኞችን መለያ እጣ ይፋ አደረገ።
በዚሁ እጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓት ላይ ከአራቱም ዙር የተወጣጡ ተመዝጋቢዎች የተካተቱ ሲሆን፣ ባለ እድለኞቹም በቦታው ተገኝተው የህልማቸውን መሳካት በደስታ ተከታትለዋል።
እንደ ተቋሙ ገለጻ፣ የወጣው እጣ የተለያዩ የክፍል አማራጮችን ያካተተ ሲሆን፦
👉45 ሰዎች የባለ አንድ መኝታ፣
👉105 ሰዎች የባለ ሁለት መኝታ፣
👉150 ሰዎች ደግሞ የባለ ሶስት መኝታ ቤቶች እድለኛ ሆነዋል።
ኪ ሃውሲንግ “Economies of Scale” የተሰኘውን የፋይናንስ ሞዴል በመጠቀም አነስተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች የቤት ባለቤት እያደረገ መሆኑን ገልፇል።
እስካሁን በአዲስ አበባ ስድስት ሳይቶች እና በባህርዳር ከተማ በመቶዎች የሚቆጠሩ አባላቱን ማስተናገዱንም አስታውሷል።
በአሁኑ ወቅት ከ20,000 በላይ አባላት ያሉት ተቋሙ፣ በቀጣይም “ኪ መንደር” የተሰኘ ግዙፍ የመኖሪያ መንደር ለመገንባት በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታውቋል።
