በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ አዳዲስ የፈጠራ ስራ ድርጅቶች (ስታርትአፕ) በተለያዩ የመንግስት እርከኖች ባሉ የተወሳሰቡና ተደራራቢ የፈቃድ አሰጣጥ ሂደቶች ሳቢያ ለከፍተኛ እንግልት እየተዳረጉ መሆኑ ተመላከተ።
ምንም እንኳን መንግስት በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አማካኝነት ለውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት አዳዲስ እድሎችን ቢፈጥርም፣ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ይወስናሉ ተብለው የሚጠበቁት እነዚህ ድርጅቶች አሁንም በቢሮክራሲ ማነቆ ውስጥ ይገኛሉ።
በዘንድሮው ዓመት መጀመሪያ ላይ የስታርትአፕ አዋጅ ቢጸድቅም፣ በመመሪያውና በተግባር ባለው አሰራር መካከል ከፍተኛ ልዩነት መኖሩን ስራ ፈጣሪዎች ይናገራሉ።
