አቶ ጀማል አህመድ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨማሪ 26 ሚሊየን ብር ሰጡ

Date:



አቶ ጀማል አህመድ ባሳለፍነው ወር ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ  ከሰጠው 50 ሚሊየን ብር ስጦታ ተጨማሪ የሚሆን  ክለባችን ያለበትን የውጪ ተጨዋቾች ደመወዝ ክፍያ፣ወለድ እና ቅጣት መክፈያ የሚሆን ተጨማሪ  26 ሚሊየን ብር  ሚያዚያ 16 ቀን 2018 ዓም ገቢ አድርገዋል፡፡

ይህንን ተከትሎም ክለባችን ያለበትን እዳ ከመክፈሉም በላይ በፊፋ የተጣለበትን የተጫዋቾች ምዝገባ እገዳ የሚነሳለት ይሆናል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ የምዝገባ እገዳው ከተነሳለት በኋላ እየተካሄደ ላለው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እና ለሚመጣው የውድድር ዘመን ተጫዋቾችን መመዝገብና ማስፈረም ይችላል፡፡

አቶ ጀማል አህመድና ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ   እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ክለባችን ቅዱስ ጊዮርጊስ በሚፈልገው ሁሉ የማይተካ ድጋፍ እያደረጉ የቀጠሉ ሲሆን ለክለቡ እድገትና ስኬት እያበረከቱ ላለው የላቀ አስተዋፅኦ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር በክለቡ እና በደጋፊዎቹ ስም የከበረ ምስጋናውን ያቀርባል።

#ይሄነውጊዮርጊሳዊነት

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በኬንያ የመንገደኞች አውሮፕላን ከመስመሩ ወጥቶ ተከሰከሰ

ዛሬ ረፋድ ላይ በኬንያ ማንዴራ የአውሮፕላን ማረፊያ አንድ...

“የቻይና-አፍሪካ የምርምር ማዕከል”በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሊከፈት ነው

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከቻይና-አፍሪካ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር "የቻይና-አፍሪካ የምርምር...

በኢትዮጵያ በማሳደጊያ ተቋማት የሚገኙ ሕፃናት ቁጥር ወደ 12 ሺሕ ዝቅ አለ

በኢትዮጵያ በተለያዩ የሕፃናት ማሳደጊያ ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ሕፃናት...

በአሰሪና ሰራተኛ የህግ ክርክር አዲስ የሰበር ውሳኔ ተላለፈ

ለተከታታይ አምስት ቀናት ከስራ የቀረ ሰራተኛ ያለማስጠንቀቂያ ከስራ ሊሰናበት...