የጀነራሉ ታደሰ እገታ እና ያሉበት ሁኔታ?

Date:

ጀነራሉ መታገታቸው ተረጋገጠ፡፡ አንድ ወር ለሚሆን ጊዜ ከአደባባይ የጠፉት ጀነራሉ፤ መታገታቸውን የፈረንሳዩ ጋዜጣ ይፋ አድርጓል፡፡

ጀነራሉ ወደ አዲስአበባ እንዳይጓዙ እና ለፌዴራል መንግስት ባለስልጣናት ጋር እንዳይገናኙ በሚል ነው የታገቱት ተብሏል፡፡

ጀነራሉ ታግተዋል፡፡ የተረጋገጠ መረጃ ነው፡፡ ህውሃት ከአንድር ወር በፊት ደብረጽዮን ገብረሚካኤልን ፕሬዝዳንት አድርጎ ጀነራል ታደሰ ላይ መፈንቅለ መንግስት ካከናወነ በኋላ፤ ጀነራሉ ጠፍተው ከርመዋል፡፡

ከዚህ የመፈንቅለ አስተዳደር በኋላ በአደባባይ ያልታዩት ጀነራል ታደሰ፤ የት ጠፉ በሚልም ብዙ ሲጠየቅ ነበር፡፡ ለዚህ ጥያቄ መልስ የሚሆን መረጃ ዛሬ ይፋ ሆኗል፡፡

ታማኙ የፈረንሳይ ጋዜጣ አፍሪካን ኢንተለጀንስ ስለ ጉዳዩ ሰማሁት ያለውን መረጃ ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡

ጀነራል ታደሰ ወረደ ከመቀሌ እንዳይወጡ እና እንዳይንቀሳቀሱ ታግተው እንደሚገኙ አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡

‹‹ጀነራሉ ወደ አዲስአበባ እንዳይጓዙ በዚያም ከፌዴራል ባለስልጣናት ጋር እንዳይገናኙ በሚል በህውሃት ቁጥጥር ስር ናቸው›› በማለት ዘግቧል፡፡

የአፍሪካን ኢንተለጀንስ ዘገባ እንደሚያመላክተው፣ ይህ እገዳ የተጣለው በጀነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤ እና ጌታቸው ረዳ አሰባሳቢነት ባለፈው ሳምንት በአዲስአበባ ምክርቤት መመስረቱን ተከትሎ ነው፡፡ የእነ ጀነራል ፃድቃን የአዲስአበባው ምክርቤት ሕውሓትን ባጭር ጊዜ አስወግዶ ክልሉን ለመቆጣጠር አቅዷል፡፡

ህውሓት ጀነራል ታደሰ ወደ አዲስአበባ ኮብልለው ከአዲሱ ምክርቤት ጋር እዳይቀላቀሉ በሚል ነው ጀነራል ታደሰን የቁም እስረኛ ያደረጋቸው ብሏል ዘገባው፡፡

ጀነራሉ ብዙ ሚስጥር የሚያውቁ እና ህውሃት አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ሰው በመሆናቸው እንደሆነ ጋዜጣው አብራርቷል፡፡

ከአፍሪካን ኢንተለጀንስ መረጃ መረዳት እንደተቻለው ህውሓት ጀነራሉን ለማገት የወሰነው በሁለት አበይት ምክንያቶች ናቸው፡፡

አንደኛው ጀነራሉ የእነፃድቃንን ምክርቤት እንዳይቀላቀሉ በሚል ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ጀነራሉ እጅ ላይ በርካታ የሕውሓት ሚስጥሮች በመኖራቸው ነው፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በ2026 የዓለም ዋንጫ ላይ ለተለያዩ ብሔራዊ ቡድኖች የሚጫወቱ ወንድማማቾች

የ2026 የፊፋ የዓለም ዋንጫ ከመላው ዓለም የተውጣጡ ምርጥ ተጫዋቾችን...

ኢንፊኒቲ ለቤትና ለመኪና መግዣ ብድር እየሰጠ እንደሚገኝ አስታወቀ

ኢንፊኒቲ ኃላፊነቱ የተወሠነ መሠረታዊ የቁጠባ እና ብድር ኀብረት ሥራ...

የአዲሱ የወንጀል ህግ ስነ-ስርዓት የእርማት ስራዎች ሳይጠናቀቁ በሥራ ላይ እየዋለ ነው

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ላለፉት 64 ዓመታት...

ናይጄሪያው ዩናይትድ ካፒታል በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የውጭ ኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ አገኘ

​የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን በሀገሪቱ የካፒታል ገበያ ታሪክ ለመጀመሪያ...