የሰላም ፈንድ ተጀመረ!

Date:


አውስትራሊያ፣ ካናዳ እና እንግሊዝ ለእስራኤል እና ፍልስጤም ግጭት የ4 ሚሊዮን ዶላር የሰላም ፈንድ ጀመሩ።

ሀገራቱ የጋራ የሰላም ፈንድ የጀመሩት የእስራኤል እና የፍልስጤም ግጭትን ለመፍታት እያንዳንዱ ሀገር 1 ሚሊየን ፓውንድ (1.34ሚሊየን ዶላር) እንዲያዋጣ በመስማማት ነው።

በትላንትናው እለት ይፋ የሆነው የፈንድ ስምምነት፥ የመጣው ሦስቱ ሀገራት ከፈረንሳይ፣ ኒውዚላንድ እና ኖርዌይ ጋር በመሆን በዚህ ሳምንት በእስራኤል ጦር በተያዘው ዌስት ባንክ በፍልስጤማውያን ላይ በገንዘብ በሚረዱ እና በሚፈጽሙት ኔትወርኮች ላይ የተቀናጀ ማዕቀብ እንደሚጣል ካሳወቁ በኋላ ነው።

የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢቬት ኩፐር በሰጡት መግለጫ፥ የመካከለኛው ምስራቅ ሰላም፣ ፍትህ እና ደህንነት በሁለት መንግስታት መፍትሄ ላይ የተመሰረተ ነው ያሉ ሲሆን፥  ለዚህም ነው ሀገሮቻችን ከእስራኤል መንግስት ጎን ለፍልስጤም ግዛት እውቅና የሰጡት ብለዋል።

ይሁንና ብዙ ጊዜ የመካከለኛው ምስራቅ ሰላም እንደ ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ጉዳይ ብቻ ነው የሚታየው ያሉት  ኩፐር፥ እስራኤላውያን እና ፍልስጤማውያን በግጭት እና በዓመፅ ውስጥ መቀጠላቸውን ጠቅሰው፥ እኛ በሁሉም ወገኖች መካከል ውይይት፣ ሰላም እና መተማመን የሚገነቡ ድርጅቶች መደገፍ አለብን ብለዋል።

ይህ ተነሳሽነት ለፍልስጤማውያን ሰብአዊ ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ በህገወጥ ሰፋሪዎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ እንዲሁም የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን ባለ 20 ነጥብ የጋዛ የሰላም እቅድን ለመደገፍ ያለመ ነው ማለታቸውን አለጀዚራ ዘግቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...