የሎጂስቲክስ ባለሞያዉ ዳዊት ውብሸት በዓለም አቀፍ የሎጂስቲክስ እና የአቅርቦት ሰንሰለት አመራር ዘርፍ እውቅና አገኙ

Date:

ኢትዮጵያዊው የሎጂስቲክስ ባለሙያው ዳዊት ውብሸት፣ በዓለም አቀፍ የሎጂስቲክስ እና የአቅርቦት ሰንሰለት አመራር ዘርፍ ባበረከቱት የላቀ አስተዋፅኦ ዓለም አቀፍ እውቅና ተሰጣቸው።

የኢትዮጵያ የጭነት አስተላላፊዎች እና የመርከብ አገልግሎት ወኪሎች ማህበር ፕሬዚዳንት እንዲሁም የብሪክስ የንግድ ምክር ቤት የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ሊቀመንበር የሆኑት ዳዊት ውብሸት፤ በ«Insights Success Media» አማካኝነት የ«Global Excellence in Logistics & Supply Chain Leadership Award 2026» ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ዳዊት እውቅናውን ያገኙት ውስብስብ የሎጂስቲክስ ሂደቶችን ወደ ውጤታማ ዕድሎች በመቀየር ዘርፉን በአመራር ብቃታቸው በማሳደጋቸው መሆኑ ተገልጿል።

በሎጂስቲክስ፣ በጭነት አስተላላፊነት እና በአቪዬሽን ዘርፍ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ልምድ ያላቸው ባለሙያው፣ በተለይም በአየር ጭነት ትራንስፖርት ላይ ያላቸው ጥልቅ እውቀት ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የንግድ መስመር ያላትን ተጽዕኖ ለማሳደግ ትልቅ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ ተመላክቷል።

ይህ ዓለም አቀፍ ሽልማት፣ የኢትዮጵያ የሎጂስቲክስ ዘርፍ ባለሙያዎች በአህጉራዊ እና በዓለም አቀፍ የንግድ ግንኙነቶች ያላቸውን የላቀ ብቃት ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።

ዳዊት በበርካታ ዓለም አቀፍ ተቋማት የቦርድ አባል በመሆን የሚያገለግሉ ሲሆን፣ በቅርቡም በአዲስ አበባ ለሚዘጋጀው ዓለም አቀፍ የሎጂስቲክስ ጉባኤ አገሪቷን በአዘጋጅነት ለማብቃት እየሠሩ እንደሚገኙ ታውቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጉምሩክ ኮሚሽን ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱን ገለጸ

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት 725.25 ቢሊዮን ብር...

ከ1.5 ሚሊዮን ዶላር የአፍሪካ ንፁህ ኢነርጂ ፈንድ አምስቱ አቅኚ የኢትዮጵያ ድርጅቶች ተመረጡ

በምስራቅ አፍሪካ የንፁህ ኢነርጂ አቅርቦትን በማሳደግ የስራ እድልን ለመፍጠርና...

ታላቅ የምስጋና እና የስጦታ መርሃ-ግብር ጥሪ!

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ባለፉት 5 ዓመታት ላበረከቱት ከፍተኛና ታላቅ...

የቀድሞዉ የኢራን ላዕላይ መሪ አያቶላሕ ዓሊ ኻምኔይ ተቀበሩ

ዩናይትድ ስቴትስና እስራኤል ባለፈዉ የካቲት ማብቂያ ላይ የገደሏቸዉ የኢራን...