ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ደንበኞች የፕሪሚየም የጉዞ ጥቅሞችን የሚያስገኝ የፕላቲንየም ብራንድ የማስተር ካርድ ይፋ አድርገዋል።
አዲሱ ካርድ ደህንነቱ የተጠበቀ ዲጂታል ክፍያን ከሼባ ማይልስ ጥቅማጥቅሞች ጋር በማቀናጀት የአየር ማረፊያ ላውንጅ አገልግሎትን ጨምሮ ልዩ የጉዞ ጥቅማጥቅሞችን ያቀርባል ተብሏል።
በፊዚካል እና በቨርቹዋል አማራጮች የቀረበው ይህ ካርድ፣ የማስተርካርድን ዓለም አቀፍ የክፍያ አቅም፣ የዳሸን ባንክ ሱፐር አፕ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድን ሰፊ የጉዞ አውታረ መረብ በአንድ ላይ አቀዳጅቷል።
ካርዱ በዳሸን ባንክ የቀረበ ሲሆን፣ በማስተርካርድ ዓለም አቀፍ የክፍያ አውታረ መረብ የሚሠራ እና ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የሎያሊቲ ፕሮግራም ከሆነው ከሼባ ማይልስ ጋር የተገናኘ ነው።
ቨርቹዋል ካርዱ በቀጥታ በዳሸን ባንክ ሱፐር አፕ በኩል እንደሚገኝ ተነግሯል።
ከ2 ሚሊዮን በላይ ንቁ ተጠቃሚዎች ያሉት ይህ ዲጂታል ፕላትፎርም ደንበኞች በቀላሉ ካርዱን እንዲያገኙና ወዲያውኑ በዲጂታል ክፍያዎች እንዲጠቀሙበት ያግዛል።
ይህም ከጉዞ ጋር የተቀናጀ የክፍያ መፍትሔ ለሚፈልጉ ደንበኞች ምቹና ፈጣን ተደራሽነትን ያቀርባል ነው የተባለው።
በአጠቃላይ፣ ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ ጉዞን፣ የደንበኛ ሎያሊቲን እና የፋይናንስ አገልግሎቶችን የሚያገናኝ ነው፡፡
