ፈረንሳይ ከሞሮኮ – የምሽቱ ጨዋታ

Date:

በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ ጥምር አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው በ2026 የዓለም ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ዛሬ ይጀምራሉ፡፡

ዛሬ ምሽት የሁለት ጊዜ የመድረኩ አሸናፊ ፈረንሳይ ከአፍሪካዊቷ ሀገር ሞሮኮ ጋር የምታደርገው ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

ፈረንሳይ በ16ቱ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ ፓራጓይን እንዲሁም ሞሮኮ አዘጋጇን ሀገር ካናዳን በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን መቀላቀላቸው ይታወሳል፡፡

በዓለም ዋንጫ ታሪክ ለግማሽ ፍጻሜ በመድረስ ብቸኛዋ አፍሪካዊት ሀገር የሆነችው ሞሮኮ በድጋሚ ግማሽ ፍጻሜውን ለመቀላቀል ብርቱ ፉክክር እንደምታደርግ ይጠበቃል፡፡

ሞሮኮ በ2022 የኳታር የዓለም ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ ግማሽ ፍጻሜ መግባቷ የሚታወስ ሲሆን፥ በወቅቱ በፈረንሳይ 2 ለ 0 መሸነፏ አይዘነጋም፡፡

በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ 7 ግቦችን በማስቆጠር ለወርቅ ጫማው እየተፋለመ የሚገኘው ፈረንሳዊው ኮከብ ኪሊያን ምባፔ በጨዋታው ልዩነት ፈጣሪ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም ማይክል ኦሊሴ፣ ኦስማን ዴምቤሌ በፈረንሳይ በኩል እንዲሁም ብራሂም ዲያዝ እና አዘዲን ኦናሂ በሞሮኮ በኩል የሚጠበቁ ተጫዋቾች ነው፡፡

ምሽት 5 ሰዓት ላይ በቦስተን ጁሌት ስታዲየም የሚደረገውን የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ አርጀንቲናዊው ዳኛ ፋኩንዶ ቴሎ ይመሩታል፡፡

የፈረንሳይ እና ሞሮኮ አሸናፊ በቀጣይ በግማሽ ፍጻሜው ከስፔን እና ቤልጂየም አሸናፊ ጋር የሚገናኝ ይሆናል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጉምሩክ ኮሚሽን ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱን ገለጸ

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት 725.25 ቢሊዮን ብር...

ከ1.5 ሚሊዮን ዶላር የአፍሪካ ንፁህ ኢነርጂ ፈንድ አምስቱ አቅኚ የኢትዮጵያ ድርጅቶች ተመረጡ

በምስራቅ አፍሪካ የንፁህ ኢነርጂ አቅርቦትን በማሳደግ የስራ እድልን ለመፍጠርና...

ታላቅ የምስጋና እና የስጦታ መርሃ-ግብር ጥሪ!

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ባለፉት 5 ዓመታት ላበረከቱት ከፍተኛና ታላቅ...

የቀድሞዉ የኢራን ላዕላይ መሪ አያቶላሕ ዓሊ ኻምኔይ ተቀበሩ

ዩናይትድ ስቴትስና እስራኤል ባለፈዉ የካቲት ማብቂያ ላይ የገደሏቸዉ የኢራን...