ብርቅዬው የዋልያ አይቤክስ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነሱ ምክንያት

Date:

ዓለም አቀፍ የተፈጥሮ ጥበቃ ሕብረት (IUCN) በቅርቡ ባደረገው ግምገማ በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኘው የዋልያ አይቤክስ ዝርያ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ማሽቆልቆሉን ተከትሎ፤ «ለመጥፋት አደጋ በእጅጉ የተጋለጠ» በሚል መደቡ ውስጥ መካተቱን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ፖል ሾልት ሾልት እንደገለጹት የተደረጉ ተጨማሪ ጥናቶች በኢትዮጵያ ስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ ብቻ የሚገኘው ዋሊያ አይቤክስ ቁጥር አሁንም እያሽቆለቆለ መሆኑን ያሳያሉ።

በታህሳስ 2017 በተካሄደ ጥናት 271 ዋልያዎች ብቻ ተገኝተዋል ብለዋል። ይህም በአንድ ዓመት ውስጥ ከፍተኛ የቁጥር ማነስ መኖሩን አመላክቷል ብለዋል።

ለዝርያው መመናመን፤ ለሥጋና ለባህላዊ መድኃኒትነት የሚደረገው ሕገ-ወጥ አደን፣ የተፈጥሮ መኖሪያ መራቆት እና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው የሰዎች ድንበር መተላለፍ ቀዳሚ ምክንያቶች መሆናቸው በጥናት ተረጋግጧል ተብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...