የአሜሪካ የታክስ ህግ የስፔንን የዓለም ዋንጫ ሽልማት ስጋት ላይ ጣለ

Date:

የስፔን ብሔራዊ ቡድን ከዓለም ዋንጫ ሊያገኘው ከሚችለው 50 ሚሊዮን ዶላር የሽልማት ገንዘብ ላይ የአሜሪካው የገቢዎች ባለስልጣን (IRS) የታክስ ድርሻ መጠየቁ አከራካሪ ሆኗል።

ውድድሩን በጋራ ያዘጋጁት ሜክሲኮና ካናዳ ለተሳታፊ ቡድኖች ሙሉ የታክስ ነፃ መብት የሰጡ ቢሆንም፣ አሜሪካ ግን “በግዛቴ ውስጥ የተገኘ ማንኛውም ገቢ ታክስ ይከፈልበታል” በሚለው ህጓ በመፅናቷ ቡድኖቹን ለከፍተኛ ክፍያ ዳርጋቸዋለች።

በመደበኛው ህግ መሰረት ከአሜሪካ በሚገኝ ገቢ ላይ 30% የታክስ ተቀናሽ የሚደረግ በመሆኑ፣ ስፔን ከ50 ሚሊዮን ዶላር የሽልማት ገንዘብ ውስጥ እስከ $15 ሚሊዮን ዶላር ልታጣ ትችላለች።

ይሁን እንጂ ትክክለኛው የታክስ መጠን የሚወሰነው ስፔን በሶስቱ አዘጋጅ ሀገራት በነበራት የጨዋታዎች ብዛት ድርሻ ነው። ይህንን ውዝግብ ለመፍታት የአሜሪካ እና የካናዳ የታክስ ተቋማት የሽልማት ገንዘቡ ታክስ እያንዳንዱ ቡድን በየሀገራቱ ባደረገው የጨዋታዎች ብዛት ተሰልቶ እንዲከፋፈል ተስማምተዋል።

የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጄኤፍኤም 106.7 የሬዲዮ ጣቢያ ለ6 ወራት ታገደ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ባደረገው የይዘት ክትትልና የኢንስፔክሽን ምልከታ...

ሱልጣን ቢን ኻሊፋ ግሩፕ በኢትዮጵያ በሆቴል ዘርፍ ሊሰማራ ነው

በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር...

ህወሓት ከሌሎች ተቃዋሚ ኃይሎች ጋር የሚደረግ ጥምረት አስፈላጊ መሆኑን ገለጸ

ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ...

አሜሪካ በኢራን ጦርነት 37.5 ቢሊዮን ዶላር ማውጣቷን የመከላከያ ሚኒስትሩ ተናገሩ

አሜሪካ በኢራን ጦርነት ወደ 37.5 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ማውጣቷን...