ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መንግሥት ጋር ተቃውሞ ካላቸው ሌሎች ቡድኖች ጋር ጥምረት መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን ገለፀ። ፓርቲው እንዲህ አይነቱን ትብብር የጋራ ሥጋትን ለመታገል የሚደረግ ወሳኝ የትግል አካል ሲል ገልጾታል።
ሕውሃት ማክሰኞ ዕለት ባወጣው ሳምንታዊ መግለጫ፤ በትግራይ ክልል በተካሄዱ ሕዝባዊ የምክክር መድረኮች ላይ ከፌደራል መንግሥቱ «ተመሳሳይ ሥጋት ከተደቀነባቸው ሌሎች ኃይሎች» ጋር ትብብር ማድረግ እንደሚያስፈልግ የጋራ መግባባት ላይ መደረሱን ገልጿል።
ሆኖም መግለጫው ድርጅቱ አብሯቸው ለመሥራት ያሰባቸውን ቡድኖች ስም አልገለጸም፤ ወይም አሁን ስላሉትም ሆነ ወደፊት ስለታቀዱ ጥምረቶች ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል።
