የኢትዮጵያ መንግሥት የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕን የውጭ እዳ ግማሽ ያህሉን ከመንግሥት በጀት ሊሸፍን መሆኑ ተነገረ።
ይህ ውሳኔ ተቋሙን ከገጠመው የፋይናንስ ውጥረት ለማውጣትና ለግል ባለሀብቶች ለማስተላለፍ ዝግጁ ለማድረግ የተነደፈ የማገገሚያ ዕቅድ አካል መሆኑ ለካፒታል የደረሰው መረጃ ያመለክታል።
ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብሩክ ታዬ እንደተናገሩት ፣ የስኳር ዘርፉ የውጭ እዳ 144 ቢሊዮን ብር (ወደ 2.1 ቢሊዮን ዶላር) ገደማ ደርሷል።
በተለይም ሳይጠናቀቁ ከፍተኛ ወጪ የጠየቁ እንደ ኦሞ ኩራዝ ያሉ ፕሮጀክቶች ለአገሪቱ የባንክ ሥርዓትና የሕዝብ ፋይናንስ ትልቅ ጫና ሆነው ቆይተዋል።
