ፍርድ ቤቱ በክረምት ተረኛ ችሎት በአስቸኳይ የሚስተናገዱ ጉዳዮችን ይፋ አደረገ

Date:

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣ በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 38 ንዑስ አንቀጽ 3 መሠረት፣ በክረምት ወቅት በተረኛ ችሎት የሚስተናገዱ አስቸኳይ የፍትሐ ብሔርና የወንጀል ጉዳዮችን ይፋ አድርጓል።

ፍርድ ቤቱ እንደገለጸው፣ ከመደበኛ የፍርድ ቤት የሥራ ጊዜ ውጭ መሠረታዊ መብቶችን የሚመለከቱ፣ በጊዜ የማይሰጡ እና አፋጣኝ ውሳኔ ካልተሰጣቸው ሊተካ የማይችል ጉዳት የሚያስከትሉ አስቸኳይ ጉዳዮች በተረኛ ችሎት ይስተናገዳሉ።

የፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ የሚሆኑበት ከነሐሴ 1 እስከ መስከረም 30 ባለው ጊዜ ተረኛ ችሎት አገልግሎት ይሰጣል።

በፍትሐ ብሔር ጉዳዮች መካከል የሚስተናገዱት፦

  • አስቸኳይ የእግድ አቤቱታዎች
  • የልጅ ቀለብ ጉዳዮች
  • አካልን ነጻ ለማውጣት የሚቀርቡ አቤቱታዎች
  • እንቅስቃሴን በሚገድቡ ጉዳዮች ላይ የሚቀርቡ አቤቱታዎች
  • ሠራተኞች በአሠሪዎቻቸው ላይ የሚያቀርቧቸው የደመወዝ ክፍያ አፈጻጸም ጥያቄዎች
  • ከግልግል ዳኝነት ትዕዛዝ ጋር የተያያዙ አስቸኳይ የማኅተም አገልግሎት ጥያቄዎች
  • ሌሎች ጊዜ የማይሰጡ አጣዳፊ ጉዳዮች።

በወንጀል ጉዳዮች ደግሞ፦

  • የዋስትና ጥያቄዎች
  • የአመክሮ ጉዳዮች
  • እስረኛ ያላቸው የወንጀል መዛግብት (RTD)
  • በሰበር የሚቀርቡ አቤቱታዎች
  • የአራዳ ምድብ ችሎት ቀጠሮዎች
  • ለመሰየም የሚቀርቡ አቤቱታዎች
  • እና መደበኛ የሥራ ጊዜን መጠበቅ የማይችሉ ሌሎች አጣዳፊ የወንጀል ጉዳዮች ይታያሉ።

በመሆኑም ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ በሚሆኑበት በዚህ ወቅት፣ ተገልጋዮችና የፍርድ ቤቱ ማኅበረሰብ አሠራሩን ተገንዝበው አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጥሪ አቅርቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር በዓለም የምግብ ምርምር ድርጅት ሹመት ተሰጣቸው

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር እና የአግራ (AGRA) የቦርድ ሰብሳቢ...

አቶ ሳሙኤል ታፈሰ በካናዳ ሀገር ሊሸለሙ ነው

የሰንሻይን ኢንቨስትመንት ግሩፕ መስራችና ሊቀመንበር አቶ ሳሙኤል ታፈሰ በንግዱ...

በምክክሩ ወቅት በሀሳብ ልዩነት “አድማ የመቱ” ነበሩ

ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በ22ኛው ቀን ውሎው በስልታዊ ቡድን ደረጃ...

በፌደራል መንግሥት እና በህወሓት መካከል ያለዉ ግጭት እንዳሳሰበው የአውሮፓ ሰላም ፋውንዴሽን ገለፀ

የአውሮፓ ሰላም ፋውንዴሽን  በኢትዮጵያ ፌደራላዊ  መንግሥት እና በህዝባዊ ወያኔ...