ከሥር ከላይ በስተግራ የምታየው ፎቶ 1 የታሪካዊዉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር ሕንፃ አሁናዊ ገጽታ ነው ቢባል ማን ያምናል? የሕንፃውን የጥበብ ማዕከልነት ያውጁ የነበሩ እነዚያ ቀለሞች ዛሬ የሉም፤ በግራጫ ቀለም ቁጥጥር ሥር ውለው ደብዛቸው ጠፍቷል።
እናም ቀደም ሲል ማንነቱን በሩቁ ያውጅ የነበረው ይህ ታሪካዊ ሕንፃ ዛሬ አፍሮና ተሸማቅቆ ራሱን በአካባቢው ባሉ ሕንፃዎች ውስጥ ለመደበቅ የሚጥር ይመስላል፤ The historial Ethiopian National Theatre building has totally blended itself with the surrounding context in the name of homogenization project! ሌላው ቢቀር ቀለሞቹን መልሷቸው።
ፈቃደኜነቱ ካለ፣ የቀለሞቹን ሙሉ ወጪና የሠራተኛ ሂሳብ ድርጅታችን ኒታ ከለር ሰንተር ይሸፍናል።
በነገራችን ላይ አርክቴክቱ ሄንሪ ሾሜት የቀለሞቹን ሕብር ያለምክንያት አላስቀመጣቸውም። የቀለማቱ ሕብር ከሥነ ውበታዊ ዓላማ ይልቅ ለ”Functionalism” የቀረቡ ናቸው፤ Just to say that the colors are functional colors!!! እናም በየትኛውም መልኩ ግራጫ ቀለም የጥበብ ማዕከል መገለጫ አይሆንም።
Getahun Heramo
