ኢትዮጵያ ስድስት የሱዳን ዲፕሎማቶች በ48 ሰዓት ውስጥ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አዘዘች

Date:

ስድስት የሱዳን ዲፕሎማቶች በ48 ሰዓት ውስጥ ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ ማዘዟን ሮይተርስ ዘግቧል።

እንደዘገባው ከሆነ ዲፕሎማቶቹ ሁለቱ ሀገራት በሚዋሰኑበት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መዲና አሶሳ በሚገኘው የሱዳን ቆንስላ ጽህፈት ቤት ይሰሩ የነበሩ ናቸው።

ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በኋላ አዲስ አበባ ከአስመራ እና ካርቱም ጋር ያላት ግንኙነት እየሻከረ መጥቷል።

ከአንድ ወር በፊት በተመሳሳይ ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ይገኙ የነበሩ 10 የኤርትራ እና አንድ የግብጽ ዲፕሎማቶች መባረራቸው ይታወሳል።

ይህን ውሳኔ ተከትሎ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር የነበራትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሙሉ ለሙሉ ስታቋርጥ ግብጽ በበኩሏ በኢትዮጵያ ላይ ተመሳሳይ የአጸፋ እርምጃ መውሰዷን አስታውቃ ነበር።

ኢትዮጵያ እና ሱዳን አንዳቸው በአንዳቸው የውስጥ ጉዳዮች ላይ ጣልቃ መግባታቸውን በተደጋጋሚ መግለጻቸው ይታወሳል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...