የጋዜጠኛ ቤተልሔም ተስፋዬ የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈጸመ

Date:

በ39 ዓመቷ በትላንትናው ዕለት በድንገት ሕይወቷ ያለፈው ታዋቂዋ ጋዜጠኛ እና የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ቤተልሔም ተስፋዬ የቀብር ሥነ ሥርዓት ዛሬ ሕዳር 7 ቀን 2019 ዓ.ም በካራ አሎ ደብረ ቀርሜሎስ መድኃኔዓለምና አቡነ ገሪማ ገዳም ተፈጸመ።

በባሌ ሮቤ የተወለደችው ቤተልሔም፤ የትምህርት ጉዞዋን በኮተቤ መምህራን ኮሌጅ በቋንቋ ዲፕሎማ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም በጋዜጠኝነትና ተግባቦት የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪዎቿን አጠናቃለች። የሙያ ሕይወቷን መስማት የተሳናቸውን ተማሪዎች በምልክት ቋንቋ በማስተማር የጀመረችው ባለሙያዋ፣ በትጋቷ እስከ ርዕሰ መምህርነት ደረጃ መድረስ ችላለች።

በቀጣይም ወደ ጋዜጠኝነትና የሕዝብ ግንኙነት መስክ በመሸጋገር በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ፣ በብሔራዊ ሥነ ሕዝብ ኢንስቲትዩት፣ በቀድሞው የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የሚኒስትሯ የኮሚኒኬሽን አማካሪ፣ እንዲሁም በሁዋዌ ቴክኖሎጂ ኩባንያ አገልግላለች። እስከ ሕልፈቷ ድረስም በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ በመሆን ሀገሯን በብቃት አገልግላለች። የቤተልሔም ድንገተኛ ማለፍ በቤተሰቦቿ፣ በወዳጆቿ፣ በሙያ ባልደረቦቿ እና በሚያውቋት ሁሉ ዘንድ ጥልቅ ሐዘን ፈጥሯል።

ቤተልሔም በሙያዊ ብቃቷ ብቻ ሳይሆን በቅንነቷ፣ በርኅራኄዋ እና የተቸገሩ ወገኖችን ለመርዳት በነበራት ታላቅ ሰብአዊ ፍቅር በብዙዎች ዘንድ በጥልቅ ትታወሳለች። ባለትዳርና የሦስት ሴት ልጆች እናት የነበረችው ወጣቷ ባለሙያ፣ በሥጋ ከዚህ ዓለም በሞት ብትለይም በሙያዋ ያበረከተችው አርአያነት ያለው አስተዋጽኦ እና በሰዎች ሕይወት ላይ ያሳረፈችው በጎ ተጽዕኖ ሁልጊዜም በመልካም ትውስታ ይኖራል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የገዛ ልጁን በአንካሴ ወግቶ ገደለ

በባልና ሚስት መካከል በተፈጠረ ጊዜያዊ አለመግባባት ምክንያት የገዛ ልጁን...

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በሆንግ ኮንግና በኔዘርላንድስ አሸነፉ

በዓለም አትሌቲክስ የፕላቲነም ደረጃ በተሰጠው የሆንግ ኮንግ ግማሽ ማራቶን...

የመንግሥት ሠራተኞች የሙያና የሥራ ባህሪ በተቀናጀ የምዘና ሥርዓት ሊመዘን ነው

የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን (FCSC) የመንግሥት ሠራተኞችን ሁለንተናዊ ብቃት...

ከሳዑዲ ዓረቢያ ከ2 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በሳዑዲ ዓረቢያ በተለያዩ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ የነበሩ 2 ሺህ...