የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ የመንግሥት ግዢን ግልጽና ከሙስና የጸዳ ለማድረግ ያወጣው አዲሱ መመሪያ ቁጥር 197/2019 ሥራ ላይ ውሏል።
በመመሪያው መሰረት ማንኛውም የቀድሞ የመንግሥት ሠራተኛ ሠርቶበት በነበረው መሥሪያ ቤት በሚወጣ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ መሥሪያ ቤቱን ከለቀቀ ከአንድ ዓመት በላይ ማለፍ አለበት።
እንዲሁም በጨረታ ሰነድ ዝግጅት ወይም በሂደቱ ውስጥ ቀጥተኛ ተሳትፎ የነበረው ሠራተኛ በምንም መልኩ በዚያ ጨረታ ላይ መሳታፊ መሆን አይችልም።
በመመሪያው ከግዢ ጋር የተያያዙ ማስታወቂያዎች፣ የሰነድ ሽያጮች እና የውል አስተዳደሮች ሙሉ በሙሉ በዲጂታል የኤሌክትሮኒክ ሥርዓት ብቻ እንዲመሩ ተደርጓል።
በጨረታ የሚሳተፉ ተቋማት ቢያንስ 10 በመቶ እና ከዚያ በላይ አክሲዮን ያላቸውን እውነተኛ ባለቤቶች ማንነት የመግለጽ ግዴታ አለባቸው ተብሏል።
አሐዱ ራዲዮ
