ኢትዮጵያ በ2026 ዓ.ም. በአፍሪካ የስንዴ ምርት ከፍተኛውን ደረጃ በመያዝ ከረጅም ጊዜ በአህጉሪቱ ቀዳሚ አምራች የነበረችውን ግብፅ ማለፏን የዘገባው መረጃ አመልክቷል።
ኢትዮጵያ የስንዴና የእህል ምርቷን በዓመት ወደ 33 ሚሊዮን ቶን ወይም ከ330 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ማድረሷን የዘገባው ጠቅሶ፣ ይህ ከግብፅ ምርት በሦስት እጥፍ ያህል እንደሚበልጥ ገልጿል።
ለዚህ የምርት ዕድገት የስንዴ ማሳን ከ8 ሚሊዮን ሄክታር በላይ ማስፋፋት፣ በክረምት ዝናብና በበጋ መስኖ እርሻ ማምረት፣ የግብርና ማሻሻያዎች፣ የ10 ዓመት የልማት ዕቅድ፣ የተሻሻሉና የአየር ንብረትን የሚቋቋሙ የዘር ዝርያዎች እንዲሁም የክላስተር እርሻ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ተጠቁሟል።
ከኢትዮጵያ በመቀጠል በአፍሪካ ከፍተኛ የስንዴ አምራች ከሆኑት ሀገራት ግብፅ ከ9 እስከ 9.7 ሚሊዮን ቶን፣ አልጄሪያ ከ3 እስከ 3.5 ሚሊዮን ቶን፣ ሞሮኮ ከ2.5 እስከ 3.5 ሚሊዮን ቶን እና ደቡብ አፍሪካ ከ2 እስከ 2.5 ሚሊዮን ቶን ምርት እንደሚያመርቱ ተዘርዝረዋል።
ይህ የምርት ዕድገት በአገሪቱ የምግብ ዋስትናን ለማጠናከር፣ የስንዴ ከውጭ ግዢ ጥገኝነትን ለመቀነስና የግብርናውን ዘርፍ ለማሳደግ እንደሚያግዝ ይጠበቃል።
