የመብት አስከባሪ እጦትና ሰቆቃው

Date:

ነቢዩ ሲራክ

በሳውዲ ድንበር ውጥረት ነግሷል …

በርካታ ስደተኞች ድንበር እያቋረጡ ነው

ታታሪው አባወራ ባልሰራው ሲወነጀል

መንግሥት ሆይ ስማን

በሳውዲ ድንበር ውጥረት ነግሷል

===========================

ከቅርብ ወራት ወዲህ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ስደተኞች የየመንና የሳውዲ አረቢያን ድንበር እየጣሱ መግባት አሳሳቢ ሆኗል ። የሳውዲ ድንበር ጠባቂዎች ድንበር በሚጥሱት ላይ ከዚህ በፊት ባልተለመደ መልኩ በድሮን እና በዘመናዊ ጦር መሳሪያ መጠበቅ ጀምረዋል ። ድንበር በሚጥሱ ላይ በተገኙበት እርምጃ እንዲወሰድ ትዕዛዝ ከተላለፈ ወዲህ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን በህገ-ወጥ መንገድ ድንበር ሲሻገሩ ተገድለዋል 😓

ከቅርብ ወራት ወዲህ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዜጎቻችን የሳውዲ አረቢያና የየመንን ድንበር መጣሳቸውን ተከትሎ የሳውዲ ጸጥታ ኃይል በተለያዩ የሳውዲ ከተሞች በኢትዮጵያውያን ላይ ያተኮረ አዲስ የእስርና የውንጀላ ዘመቻ ጀምረዋል። ዘመቻው ያተኮረው ህጋዊ መኖሪያ ፈቃድ ያላቸውንና በምንም ወንጀል ያልተሳተፉ ሰላማዊ ነዋሪዎችን ላይ ያነጣጠረ መሆኑን ተረድቻለሁ ። በምንም ወንጀል ተሳታፊ ያልሆኑ ህጋዊ ነዋሪዎችን በሰበባ ሰበብ በመያዝ አስሮና ወንጅሎ ወህኒ የመወርወር ዘመቻው በሪያድ ኢንባሲና በጅዳ ቆንስል መ/ቤት በሰፊው የሚታወቅ መሆኑን በአዲሱ ዘመቻ ዙሪያ ካሰባሰብኩት መረጃ ማረጋገጥ ችያለሁ ።

🔴 ወንጅሎ ወህኒ የመወርወር ዘመቻ ‼️

==========================

” ዲፕሎማቶች መረጃው አላቸው “

==========================

“ከወራት በፊት በጀመረው ህጋዊ ነዋሪዎችን አስሮና ወንጅሎ ወህኒ የመወርወር ዘመቻ ከጀመረ ቆይቷል” ያሉኝ በሪያድ ኢንባሲ አንድ ጉዳይ ፈጻሚ ስለሁኔታው ሲያስረዱ” ነዋሪው ዘመቻውን እስካሁን የተረዳው አይመስለኝም ። በተለያዩ ጊዜያት ወደ ሀገር ቤት የሚገቡ ታሳሪዎችን ልመዘግብ ወደ እስር ቤቶች ስሄድ ያገኘኋቸው ታሳሪዎች እንዳስረዱኝ ብዙ የእኛ ዜጎች በአየር መንገድ ሰው ለመሸኘት ብለው ፣በገበያ አዳራሾች፣ በመንገድ እና በተለያዩ ቦታዎች በፖሊስ ተይዘው ፍርድ ለአመታት ወህኒ እንዲወረወሩ ውሳኔ እንደተላለፈባቸው እያዘኑና እያለቀሱ አስረድተውኝ ያውቃሉ ።” ሲሉ ምስክርነታቸውን ሲሰጡኝ ማንነታቸውን እንዳልገልጽ ተማጽነውኛል ።

ሌላው በጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት ወዳጀን ስለ ዘመቻው የሚያውቁት ነገር አለ ? ብየ ጠይቄያቸው ” … በእስር የማዋከቡ ዘመቻ በህጋዊ ነዋሪም ላይ ከተጀመረ ቆይቷል ። ነብዩ አንተማ ታውቀው የለ … ለማን አቤት ትላለህ ? ” በማለት ጅዳ ሽሜሲ ወህኒ ለስራ በሄዱበት አጋጣሚ የመኖሪያ ፈቃድ የያዙ እጅግ ብዙ ሰላማዊ ነዋሪዎች ያለ ምንም ጥፋት ተይዘው የመንግሥት ያለህ እያሉ እንደ ማየት የሚያስከፋ ነገር የለም …

” በጅዳ ቆንስል መ/ቤት በኩል በተለይ ኢትዮጵያውያንን ህጋዊ ነዋሪዎችን ድንገት በመያዝና በመወንጀል የተጀመረው ዘመቻ የሚታወቅ ቢሆንም ጉዳዩን ለሳውዲ አረቢያ መንግሥት አሳውቆ ዜጎችን መብት ማስከበር ዛሬም አቅም ያለው ዲፕሎማት የለንም ” ሲሉ በምሬት ሲያስረዱኝ እኔም እውነቱን ተረድቸ ዜጎች ከፍተኛ ጥንቃቄ ያደርጉ ዘንድ መልዕክት አስተላልፍ ዘንድ ተማጽነውኛል።

🔴 የጎልማሳው አባወራ እጣ ፈንታ 😓

=========================

ከወራት በፊት በሳውዲ የጸጥታ ኃይሎች በተጀመረው አስሮ ማዋከብ እና ወንጅሎ ወህኒ የመወርወር ዘመቻ ሰለባ ከሆኑት መካከል የእዮሲ አባት የተባሉ አንድ ጎልማሳ አባወራ ይገኙበታል ። የእዮሲ አባት ቤተሰቦች መካከል ባለቤታቸው እንዳስረዱኝ መረጃ ባለቤታቸው ባልዋሉበት በፖሊስ ተወንጅለው ወህኒ ከተጣሉ ሁለት ወራት ሆኗል ሲሉ ጉዳዩን ማስረዳት ይጀምራሉ ።

” ባለቤቴ በህጋዊ መኖሪያ ፈቃድ ሳውዲ አረቢያ ጅዳ መኖር ከጀመረ 11አመታት ሆኗል ። ትዳር መስርተን ልጆች ወልደን ስንኖር ከጧት እስከ ማታ በስራ ተጠምዶ እየሰራ ቤተሰብ ሲያስተዳድር የሳውዲን ማናቸውም ህግ አክብሮ ነው የኖረው ። ከሁለት ወራት በፊት ይኖርበት ከነበረበት የጅዳ ከተማ በደማም ፖሊስ ተጠርቶ ሄደ ። እኛም ንጹህ መሆኑን ስለምናውቅ ለጥያቄ ተፈልጎ ይሆናል በማለት ዝም አልን ። ወደ ደማም ከሄደበት ቀን ጀምሮ ስልኩ ተዘጋ ። አድራሻው ሲጠፋን ወደ መስሪያ ቤቱ ምን ተፈጠረ ብለን ጠየቅን ። መስሪያ ቤቱም ፖሊሶች በወንጀል ጠርጥሮ ለምርመራ እንደተያዘ አሳወቁን። ከሳምንታት ቆይታ በኋላ ባለቤቴ” ወንጀል ከሰራ ሰው ጋር የመኖሪያ ፈቃድ ፎቶው ይመሳሰላል ” ተብሎ እንደሆነ ስንሰማ ጉዳያችን በጅዳ ለኢትዮጵያ ቆንስል መ/ቤት ጉዳዩን እንዲከታተልልን አቤቱታ አቀረብን ። ከወር በኋላ ባለቤቴን ፍርድ ቤት አቅርበው በጊዜ ቀጠሮ ካቆዩ በኋላ ያለ ምንም ማስረጃ የጥፋተኛነት ውሳኔ አሳልፈው ወህኒ ተወርውሯል 😓” በማለት የተገፊው ባለቤት አስረድተውኛል ።

ሌላው የቤተሰብ አባል ስለ ጉዳዩ ሲያስረዱ “*ወንጀል ተሰራ ተብሎ በተጠቀሱት ቀናት ወንድማችን ጅዳ በሚገኝ ኩባንያ ጧት ወደ ስራ ሲገባ የጣት አሸራው እያለና በዚያው ቀን ስራውን ያስረከበባቸው ሰነዶች በኩባንያው እያለ እግሩ ረግጦት በማያውቅበት ከተማ ምንም በማያውቀው “ወንጀል ሰርቷል” ተብሎ ወህኒ እንዲወርድ ተደርጓል ። ” ሲሉ ፍትህ አስከባሪ ባለመኖሩ ግፍ መፈጸሙን በምሬት አስረድተውኛል።

የተገፊው ቤተሰቦች ፍትህ ፍለጋ ወደ ጅዳ ቆንስል በመቅረብ ” ወንጀል ሰራ ባሉት ጊዜ ጅዳ መደበኛ ስራውን እየከወነ እንደነበር ለዚህ ማስረጃው በመ/ቤቱ ያለውን የጣት አሻራ ለፍርድ ቤት አቅርቡልን ” ብለው በመማጸን ተደጋጋሚ የመብት ማስከበር ጥያቄን ለጅዳ ቆንስል መ/ቤት ዲፕሎማቶች አቤቱታ አቅርበዋል። የቆንስል መ/ቤት ግን ለጉዳዩ ትኩረት ባለመስጠት ደማም ኮሚኒቲ እንዲከታተለው ደብዳቤ እንደጻፉና ” ጠበቃ ቅጠሩ” ከማለት ያለፈ መልስ አላገኙም ።

ታታሪው አባወራ ባልሰራው በማያውቀው ወንጀል ሲወነጀል የዜጋ መብቱን ለማስከበር የጅዳም ቆንስልም ሆነ በሪያድ ኢንባሲ በኩል የተሰራ ስራ የለም የሚሉት ቤተሰቦች አሁንም ባሉት ጥቂት ቀናት የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሪያድ – ሳዑዲ ዓረቢያ የበላይ ኃላፊ ዶር ሙክታር ከድር ፣ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት፤ ጄዳ Ethiopian Consulate General, Jeddah ኃላፊ አምባሳደር ጣፋ ቱሉ , MFAEthiopia Amharic የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት እየተፈጸመ ላለው በደል ትኩረት ሰጥተው አስቸኳይ መፍትሔ ይፈልጉ ዘንድ መልዕክት አስተላልፈዋል።

📍 ልብ በሉ ያ በህጋዊ መንገድ ስራውን ሲከውን ያለ ወንጀሉ ወንጀለኛ የተባለ ጎልማሳ የቤተሰብ ደጋፊ እና አስተዳዳራ ንጽህናውን አስረጅ የጣት አሻራ እና ተዛማጅ ሰነድችን ደማም ለሚገኘው ፍርድ ቤት የሚያቀርብለት የሀገሩ መንግሥት ተወካይ አጥቶ ለአመታት ወህኒ ሊወረወር ይግባኝ ማቅረቢያው ከቀናት በኋላ ያበቃል 😓

🔴 መንግሥት ሆይ ስማን ‼️

====================

📌 የዜጎችን መብት ገፈፋ አስቁሙልን ‼️

==========================

በሳውዲ አረቢያ በህጋዊና ሰላማዊ ነዋሪ ዜጎች ላይ ክብራችን የማይመጥን በደል እየተፈጸመ ነው😡 ዜጎች በስደት መብት አስከባሪ ተወካይ ዲፕሎማት አጥተዋል ። በሰቆቃ ላይ የሚገኘውን ወገን የድረሱልን ድምጽ እያሰማ ነው ።

የተገፊ ዜጋችን በደል ትሰሙት ዘንድ አንዱ ፈጣሪ አምላክ እዝነ ልቦና ይሰጣችሁ 🙏

ሌላ ምን እላለሁ …

ነቢዩ ሲራክ

ሚያዝያ 2 ቀን 2017 ዓም

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...