“የቆንስላ ኦፊሰሮች ያለፈውን የጉዞ ታሪክ እና ጥፋቶች ማየት ስለሚችሉ ማምለጥ የሚችሉበት መንገድ የለም” – በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ

Date:

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በሰጠው ማስጠንቀቂያ ከተፈቀደላቸው የቆይታ ጊዜ በአሜሪካ የሚቆዩ ሰዎች ድጋሚ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ መደረግን ጨምሮ የህግ ተጠያቂነት እንደሚያስከትል ይወቁ ብሏል።

የቆንስላ ኦፊሰሮች ያለፈውን የጉዞ ታሪክ እና ጥፋቶች ማየት ስለሚችሉ ማምለጥ የሚችሉበት መንገድ የለም ነው ያለው።

ከዚህ ቀደም በአምባሳደሩ ኤርቪን ማሲንጋ አማካኝነት በህገወጥ መንገድ ወደ አሜሪካ መግባት፣ ቪዛ ለማግኘት መዋሸት፣ ያለ ህጋዊ የስራ ፍቃድ ስራ መስራትና የቪዛ ጊዜ ካበቃ በኋላ በአሜሪካ መቆየት ከባድ ቅጣት ያስከትላል ሲል ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ እንደነበር ይታወሳል።

ይህን መሰል ማስጠንቀቂያ በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ሀገራት የሚገኙ ኢምባሲዎችም በተመሳሳይ ይህንን ማስጠንቀቂያ እየሰጡ ይገኛሉ።

የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ኃላፊ ማርክ ሩቢዮ “ከቀናት በፊት አሜሪካን መጎብኘት በነጻ የተሰጠ አይደለም። ይሄ ሕጎቻችንን እና እሴቶቻችንን ለሚያከብሩ ሰዎች የተሰጠ ልዩ መብት ነው” ሲሉ ገልጸው ነበር።

@Tikvahethmagazine @tikvahmagbot

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አሜሪካ ለኢራን ከፍተኛ ባለሥልጣን ደብዳቤ ላከች

የአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ ለኢራን ብሔራዊ ደኅንነት ምክር...

ዓመታዊ ግብርን ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ማሳወቅና መክፈል የሚያስችል አዲስ አሰራር ተዘረጋች

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ እንዳስታወቀው፣ ከእንግዲህ የደረጃ «ሀ» ግብር...

62ኛው የባህል ማዕከል ምሽት አንጋፋዋን ጋዜጠኛ የመዓዛ ብሩን ዘክሯል

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል፥ በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ታሪክ...

በኢትዮጵያ ውስጥ የህፃናት የአዕምሮ ሀኪም ቁጥር አራት ብቻ ናቸው

በኢትዮጵያ ውስጥ የህፃናት የአዕምሮ ህክምና አገልግሎት በሰፊው እንደሌለ እና...