ከ600 ሺሕ በላይ ጉዳዮችን በመመልከት ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት አስታወቀ

Date:

በ2017 በጀት ዓመት 9 ወራት ውስጥ ከ600 ሺሕ በላይ ሰነዶችን በማስተናገድና አረጋግጦ በመመዝገብ ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት አስታውቋል።

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ሐሚድ ኪኒሶ ለአሐዱ እንደገለጹት፤ በ2016 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከ700 ሺሕ በላይ ሰነዶችን በማረጋገጥና በመመዝገብ ከ2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቦ ነበር፡፡

በዚህም ዘንድሮ ከአገልግሎት አንፃር ከባለፈው አመት ጋር ተቀራራቢ ቢሆንም ግን የቀነሰበት አግባብ መኖሩን የገለጹ ሲሆን፤ ሊቀንስ የቻለበት ምክንያትም የአገልግሎት ዝውውር መቀነስ ጋር ተያያዞ የመጣ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

ከዚህ ባሻገር አገልግሎቱ የብድርና የስጦታ ውል፣ የሽያጭ እንዲሁም የውክልና ሰነዶችን የማረጋገጥና የመመዝገብ ሥራ እንደሚሰራ ያነሱት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ተደራሽነቱን ለማስፋት በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በዚህም መሠረት በዘንድሮው ዓመት ሁለት አዳዲስ ቅርንጫፎችን በመክፈት አጠቃላይ በአዲስ አበባና ድሬዳዋ በ17 ቅርንጫፎች አገልግሎቱ እየተሰጠ ይገኛል ብለዋል።

ከእነዚህም ውስጥ አፋጣኝ ምላሽ ማግኝት ያለባቸው ሰዎች በልዩነት የሚስተናገዱበትና ልዩ አገልግሎት የሚሰጡ ሦስት ቅርንጫፎች መመቻቸታቸውን አስታውቀዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ታጣቂ ኃይሎች ብቻቸውን የሚፈጽሙት ሳይሆን በመንግሥት ውስጥ ያሉ ኃላፊዎችም ጭምር …

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ከምሥረታው አንስቶ ባለፉት 7...

ከቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የተሰጠ የኀዘን መግለጫ

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በአርሲ ዞን ጥቅምት 10 እና...

 የ2026 የባሎንዶር ሽልማት አሸናፊዎች ይፋ ሆኑ!

በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፓሪስ ውጪ በለንደን በተካሄደው ታላቅ የሽልማት...

አይበገሬው ፍቃዱ —-  ( ከጋዜጠኛ ሁሴን ከድር )

ትናንት ( ቅዳሜ ጥቅምት 14 2019 ዓ.ም ) የቀድሞ...