ኢትዮጵያ እና የዩሮ ቦንድ አበዳሪዎች ውይይቶችን ለመቀጠል ተስማሙ

Date:

ኢትዮጵያ እና የዩሮ ቦንድ አበዳሪዎች በኢትዮጵያን የእዳ አስተዳደር ዙሪያ ተጨማሪ ውይይቶችን ለማድረግ ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የዓለም ባንክ ግሩፕ እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ዓመታዊ የፀደይ ወቅት ስብሰባ በዋሺንግተን ዲሲ መካሄዱ የሚታወቅ ሲሆን፤ በዚህም በገንዘብ ሚኒስትር አቶ አሕመድ ሽዴ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ከኢትዮጵያ የዩሮ ቦንድ አበዳሪዎች ጋር ተወያይቷል።

ውይይቱ እ.አ.አ ማርች 2025 ከኢትዮጵያ አበዳሪዎች ኮሚቴ በቡድን 20 አባል አገራት የዕዳ ማቃለያ ማዕቀፍ አማካኝነት በኢትዮጵያ የእዳ አስተዳደር ድርድር የተደረሰው ስምምነት ያለበት ደረጃ ላይ ትኩረቱን አድርጓል።

በዚህም ውይይት ላይ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ፤ ለንግድ አበዳሪዎቹ የኢትዮጵያን የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ሂደትን አስመልክቶ ገለጻ አድርገዋል።

ልዑኩም ሁሉን አቀፍ ሪፎርሞቹን ተከትሎ ያለውን የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሁኔታ አስመልክቶ ተወያይቷል።

በዚህም መሠረት የኢትዮጵያን የእዳ አስተዳደር አስመልክቶ የሚደረጉ ድርድሮች በተቀመጣላቸው ጊዜ እና ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማጠናቀቅ፤ ሁለቱ ወገኖች ውይይቱን ለመቀጠል መስማማታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘኘው መረጃ ያመላክታል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጥቃት አድራሹ ከካሊፎርኒያ መሆኑን ትራፕ ገለፁ

ትናንት ቅዳሜ ምሽት በዋይት ሃውስ የጋዜጠኞች ማኅበር የእራት ግብዣ...

በኬንያ የመንገደኞች አውሮፕላን ከመስመሩ ወጥቶ ተከሰከሰ

ዛሬ ረፋድ ላይ በኬንያ ማንዴራ የአውሮፕላን ማረፊያ አንድ...

አቶ ጀማል አህመድ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨማሪ 26 ሚሊየን ብር ሰጡ

አቶ ጀማል አህመድ ባሳለፍነው ወር ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ  ከሰጠው...

“የቻይና-አፍሪካ የምርምር ማዕከል”በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሊከፈት ነው

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከቻይና-አፍሪካ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር "የቻይና-አፍሪካ የምርምር...