“ቤቶች ድራማ በአዲስ መንገድ ይመጣል” አርቲስት ጥላሁን ጉግሳ

Date:

ላለፉት 12ዓመታት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በመታየት ላይ የዘለቀው “ቤቶች” ሲትኮም ድራማ 12ተኛ ዓመት እና 500ቶኛ ክፍል መነሻ አድርጎ መሰንበቻ ከድራማው ደራሲ፣ ዳይሬክተር እና ፕሮዲውሰር አርቲስት ጥላሁን ጉግሳ ጋር ቆይታ አድርጓል።

በድራማው ውስጥ የይበቃል ገፀ ባሕሪን ወክሎ ይጫወት የነበረው የአሸናፊ ማህሌት ከድራማው መውጣት እና የተዋናይት ሰብለ ተፈራ ድንገተኛ ሞት በፈተናዎቹ መካከል እንደሚጠቀስ አርቲስት ጥላሁን ጉግሳ በቆይታ አንስቷል።

ድራማውን በጀመርንበት መጨረስ አለብን ባልነው መሰረት የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ከህዝብ ጋር እንድንገናኝ መሰረት ስለጣለልን አመሰግናለሁ ሲል ገልጿል።

በቀጣይም ከ500ተኛ ክፍል በኋላ በድራማው ዙሪያ የተለየዩ ነገሮችን አስጠንተን በልዩ መልኩ ቀይረን እንመጣለን ሲል አርቲስት ጥላሁን ጉግሳ ተናግሯል።

በጥናት ሂደቱ ውስጥም በርካታ የጥበብ ባለሙያዎች፣ የቲያትር ተማሪዎችን ጨምሮ ከተመረጡ ባለሙያዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ድራማው በልዩ መልኩ ተወዳጅነቱን አስጠብቆ የመጓዝ እቅድ እንዳለም በተጨማሪነት አስታውቋል።

ኤፍ.ኤም.አዲስ 97.1

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...

የተጀመሩ የትምህርት ሪፎርሞችን በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም በቁርጠኝነት መስራት ይገባል

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን ሩብ...

የአዉሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የቡና ገበያ መዳረሻዎች እየፈለገ ነዉ

በፈረንጆቹ 2023 የፀደቀው የአውሮፓ ህብረት የደን ጭፍጨፋ ህግ ምርቶች...