🚨ከዛሬ ግንቦት 6 / 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት የኩፍኝ ክትባት ይሰጣል

Date:


ወላጆች ልጆቻችሁን አስከትቡ።

ኩፍኝ ምንድነው ?

ኩፍኝ በሽታ የኩፍኝ ቫይረስ በሚባል ረቂቅ ተህዋስ የሚከሰትና በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው የሚዛመት የበሽታ ዓይነት ነው፡፡ የኩፍኝ በሽታ ለብዙ ህጻናት ህመም፣ የአካል ጉዳትና ሞት ምክንያት ከሆኑት በሽታዎች አንዱ ነው፡፡

የበሽታው መተላለፊያ መንገዶች ምንድናቸው ?

➡️ ኩፍኝ በሽታ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው የኩፍኝ በሽታ ከተያዘው ሰው አፍንጫና ጉሮሮ በሚወጡ ፈሳሽና ጠብታዎች ንክኪና በትንፋሽ አማካኝነት ነው፡፡

➡️ የኩፍኝ በሽታ አምጭ ተህዋስ ወይም ቫይረስ በኩፍኝ ከተያዘዉ ሰዉ በከፍተኛ ሁኔታ የመሰራጨት አቅም የሚኖረው የበሽታው ምልክቶች መታየት በሚጀምርበት ወቅት ነው፡፡

➡️ አንድ በኩፍኝ የተያዘ ሰው በአብዛኛው ጊዜ ቫይረሱ ወደ ሰውነቱ ከገባ በኋላ የሽፍታ ምልክቶች በሰውነቱ ከመውጣቱ ከ4 ቀናት በፊት እንዲሁም ሽፍታዎቹ ከወጡ በኋላ እስከ 4 ቀን ድረስ ባለው ጊዜ በሽታውን ወደ ሌሎች ሰዎች በከፍተኛ ሁኔታ ያስተላልፋል፡፡

➡️ ህጻናት በሚሰባሰቡበት ቦታ ማለትም በትምህርት ቤቶች፣ በጤና ተቋማት እና በሌሎችም ቦታዎች በሽታው በቀላሉ ሊዛመት ይችላል፡፡

የበሽታው ዋና ዋና ምልክቶች ምንድናቸው ?

– ከፍተኛ ትኩሳት፣
– ከራስ ፀጉር ጀምሮ ወደ ሌሎች የሰውነት፣ ክፍሎች የሚዛመት ሽፍታ፣
– የአይን መደፍረስ ወይም መቅላት፣
– ከአፍንጫ የሚወጣ ፈሳሽ መብዛት፣
– የአይን እንባ ማዘል፣
– ሳል እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

ስላ ኩፍኝ መከላከያ ክትባት ፦ የኩፍኝ መከላከያ ክትባት ህፃናት ከተወለዱ በ9 እና በ15 ወር ዕድሜያቸው በመደበኛው የክትባት አገልግሎት ይሰጣል፡፡

በተጨማሪም የኩፍኝ ክትባት የህፃናትን በሽታ የመከላከል አቅም ለማዳበር በተለያዩ ጊዜያት በዘመቻ ይሰጣል፡፡

የኩፍኝ በሽታን በዘላቂነት መከላከል የሚቻለው ህፃናትን በመደበኛ የክትባት መርሐግብር እና በዘመቻ መልክ የሚሰጠውን የኩፍኝ በሽታ መከላከያ ክትባትን ማስከተብ ሲቻል ነው፡፡

ልጅዎትን ያስከትቡ !!

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጄኤፍኤም 106.7 የሬዲዮ ጣቢያ ለ6 ወራት ታገደ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ባደረገው የይዘት ክትትልና የኢንስፔክሽን ምልከታ...

ሱልጣን ቢን ኻሊፋ ግሩፕ በኢትዮጵያ በሆቴል ዘርፍ ሊሰማራ ነው

በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር...

የአሜሪካ የታክስ ህግ የስፔንን የዓለም ዋንጫ ሽልማት ስጋት ላይ ጣለ

የስፔን ብሔራዊ ቡድን ከዓለም ዋንጫ ሊያገኘው ከሚችለው 50 ሚሊዮን...

ህወሓት ከሌሎች ተቃዋሚ ኃይሎች ጋር የሚደረግ ጥምረት አስፈላጊ መሆኑን ገለጸ

ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ...