ኢትዮጵያ የደረሰችበትን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ለዓለማቀፉ ማሕበረሰብ የምታሳይበት የ ቴክኖሎጂ ኤክስፖ

Date:

በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አዘጋጅነት ከከግንቦት 8 እስከ 10፣2017 ዓ.ም ድረስ በአዲስ ኮንቬንሽን ማዕከል ይካሄዳል።

ኤክስፖዉ በሚኖረዉ ቆይታ የቴክኖሎጂዉን ሥነ ምህዳር ማስፋት ብሎም በዘርፉ ትብብር ማድረግ በሚቻልበት ዐውድ ዙሪያ ዉይይቶች ይካሄዳሉ።

በሁነቱ የመጀመሪያ ቀን ውሎ የሳይበር ደህንነት መሠረተ ልማት፣ ጥበቃ እንዲሁም በዘርፉ ሊቀረፉ ስለሚገባቸዉ ችግሮች ጥልቅ ዉይይቶች ይኖራሉ።

በሁለተኛዉ ቀን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የአፍሪካን የዲጂታላይዜሽን ጉዞ  ለማሳካት ያለዉን አስተዋጽኦ የሚያመላክቱ ዉይይቶች ይካሄዳሉ። የኤክስፖዉ ተሳታፊ በሆኑ ዓለማቀፍ የዘርፉ ባለድርሻዎች መካከል የልምድ ልዉዉጦችም ይደረጋሉ፡፡

አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን ከዓለማቀፍ፣ ከአህጉራዊ እና ቀጠናዊ ሁኔታዎች አንጻር የሚተነትኑ ጥናታዊ ጽሁፎች ይቀርባሉ፡፡ ሌላው የሁነቱ ድምቀት ስድስት መቶ ሺህ የኢትዮጵያ ብር ለአጠቃላይ አሸናፊዎች የቀረበበት የሮቦቲክስ ውድድር ቀጠሮ ተይዞለታል። በዚህ ዓለማቀፍ ኤክስፖ የዘርፉ ባለሙያዎች፣ ጀማሪ የቴክኖሎጂ ተቋማት እና ፖሊሲ አዉጪዎችን ጨምሮ ከ10 ሺህ በላይ ታዳሚያን ይሳተፉበታል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጄኤፍኤም 106.7 የሬዲዮ ጣቢያ ለ6 ወራት ታገደ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ባደረገው የይዘት ክትትልና የኢንስፔክሽን ምልከታ...

ሱልጣን ቢን ኻሊፋ ግሩፕ በኢትዮጵያ በሆቴል ዘርፍ ሊሰማራ ነው

በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር...

የአሜሪካ የታክስ ህግ የስፔንን የዓለም ዋንጫ ሽልማት ስጋት ላይ ጣለ

የስፔን ብሔራዊ ቡድን ከዓለም ዋንጫ ሊያገኘው ከሚችለው 50 ሚሊዮን...

ህወሓት ከሌሎች ተቃዋሚ ኃይሎች ጋር የሚደረግ ጥምረት አስፈላጊ መሆኑን ገለጸ

ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ...