ጉግል በአፍሪካ ንግድን ማሳደግ የሚያስችል የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መተግበሪያ አበለጸገ

Date:

ኤ.አይ ማክስ የተሰኘው መተግበሪያ  ትናንሽ የአፍሪካ ንግዶችን ለማስተዋወቅ አቅም ይፈጥራል ተብሏል።

ጉግል ጄምናይን ጨምሮ በተለያዩ የኤ.አይ ሞዴሎች ላይ የሚሰራው መተግበሪያው፣ የንግድ ተቋማት በፍለጋ ውጤቶች (search result) ውስጥ ያላቸውን እይታ እንደሚጨምር ዲግዋች በድረገጹ አስነብቧል።

መተግበሪያው በተጠቃሚዎች የሚፈለጉ ቃላትን በቀላሉ በማመሳሰልና አሁናዊ የሆኑ የጽሁፍ ማስታወቂያዎችን በማዘጋጀት ስማርት የሆነ የማስታወቂያ ዘዴዎችን ይጠቀማል።

በዚህም ኤ.አይ ማክስ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ወሳኝ ድጋፍ በመስጠት የአፍሪካን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ያግዛል ተብሏል።

መተግበሪያው የስራ ፈጣሪዎች ከፍላጎታቸው ጋር የሚጣጣምና ከጊዜ ወደ ጊዜ ፉክክር ባለው የዲጂታል ገበያ ውስጥ ያላቸውን ተወዳዳሪነት የሚያሻሽል መሆኑንም የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲቱት ድረገጽ አስነብቧል፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...

ፍልውሃ እና ሶደሬ!

ከሐዉለት አህመድ በቀደም ከብዙ ዓመታት በኋላ የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ሔጄ...