ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በደቡባዊ ጋዛ ካን ዮኒስ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ላይ በተፈፀመ የአየር ጥቃት ሁለት ሰራተኞቹ መገደላቸውን አስታውቋል።
በ X ገጹ ላይ በሰጠው መግለጫ፣ ሁለቱም ሰዎች የተገደሉት በቤታቸው ላይ ባነጣጠረ የአየር ጥቃት መሆኑን ገልጿል።
“በሁለት ውድ ባልደረቦቻችን ሞት ልባችን ተሰብሯል” ሲል ገልጿል።
ቀይ መስቀል በጋዛ ከፍተኛ የንፁሀን ዜጎች ሞት እንዳለ በመጥቀስ፤ የደረሰዉን ጥቃት አውግዞ አፋጣኝ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪውን አቅርቧል።
የእነሱ ግድያ በጋዛ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የሲቪል ሰዎች ሞት እንዳለ ይጠቁማል ያለዉ ድርጅቱ፤ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪያችንን በድጋሚ እናቀርባለን ብሏል፡፡
የተኩስ ማቆም እንዲደረግ የሕክምና፣የሰብአዊ እርዳታ እና የሲቪል መከላከያ ሰራተኞችን ጨምሮ ለሲቪሎች ክብር እና ጥበቃ ሊደረግ ይገባል ሲል አሳስቧል፡፡
የተባበሩት መንግስታት የፍልስጤም ስደተኞች ኤጀንሲ ከዚህ በፊት እንደገለጸዉ፤ ከጥቅምት 7 2023 ጀምሮ በጋዛ ከ2መቶ80 በላይ የራሱን ሰራተኞች ጨምሮ፤ቢያንስ 4መቶ8 የሰብአዊ ድጋፍ ሰራተኞች ተገድለዋል፡፡
